Popular Posts

Sunday, April 9, 2017

ኢየሱስን መምሰል የመጨረሻው የህይወት ግብ

እግዚአብሄር የፈጠረን በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መልክ ከሰው ውስጥ የጠፋው ሰው በሃጢያት ወደቀበት ጊዜ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ የሃጢያታችንን ሁሉ እዳ የከፈለው ወደ እግዚአብሄር መልክና አምሳል አንድንመለስ ነው፡፡የሰው ልጅ በምድር ላይ የመጨረሻው ግንብ ኢየሱስን መምሰል ነው፡፡ ለክርስቶስ ተከታይ ኢየሱስን ከመምሰል ያለፈ ግብ የለም፡፡
የእግዚአብሄር አላማ እኛ ኢየሱስን እንድመስል ነው፡፡
ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ሮሜ 8፡29
ከአስተሳሰባችን ጀምሮ ክርስቶስን አንድመስል ተጠርተናል፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ፊልጵስዩስ 2፡5
ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ እርሱን በፍፁም አንድንከተል ምሳሌ ትቶልናል፡፡
እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና። ዮሃንስ 13፡15
የክርስትያንነት መመዘኛው ኦየሱስ በምድር እንደተመላለሰ መመላለስ ነው፡፡
በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል። 1ኛ ዮሐንስ 2፡6
የትምህርት የስብከትና የማንኛውም አገልግሎት ግብ ሰዎች ክርስቶስን እንዲመስሉ ማስቻል ነው፡፡
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ ቆላስይስ 1፡28
በምድር ላይ ስንኖር ቃሉን በመቀበላችን የሚያልፍብን አስቸጋሪ ነገር ሁሉ አላማው ክርስቶስን አንድንመስል ማስቻል ነው፡፡
ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡6
በቤተከርስትያን የተሰጡት አምስቱ የአገልግሎት ስጦታዎች አላማ እኛን ወደ ክርስቶስ ሙላት ማድረስ ነው፡፡
ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ኤፌሶን 4፡12-13
የእውነተኛ አገልጋይ ሸክም ክርስቶስን በሰዎች ልብ መሳል ነው፡፡ የአገልጋይ የመጨረሻው ስኬት ክርስቶስ በልባቸው የተሳሉ ሰዎችን ማፍራት ነው፡፡
ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል። ገላትያ 4፡19
የአገልጋይ ስኬት መለኪያው ክርስቶስ የተሳለባቸው ፣ ክርስቶስን የሚሸቱና ክርስቶስን የሚመስሉ ሰዎችን ማፍራት ነው፡፡
እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡3
የአገልጋይ ታላቁ ሃላፊነት በኑሮ ክርስቶስን መስሎ ሌሎች ክርስቶስን አንዲመስሉ ምሳሌ መሆን ነው፡፡
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡1
በምድር ላይ ኢየሱስን ከመምሰል ጋር የሚጠጋ ምንም ክብር የለም፡፡ ኢየሱስን መምሰል በምድር ላይ ምንም ዋጋ የምንከፍልለት ታላቅ ግብ ነው፡፡  
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ ፊልጵስዩስ 3፡8-9
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ጌታ #መከተል #ክርስቶስእስኪሳል #መምሰል #ክርስቶስንመምሰል #ቃል #ተማሪ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #ተከታይ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment