Popular Posts

Wednesday, April 12, 2017

ተፈፀመ!

ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። ዮሐንስ 19፡30
ኢየሱስ የሰው ልጆችን የሃጢያት እዳ ለመክፈል በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ ይህን ጊዜ ነው ተፈፀመ ያለው፡፡ ግን ተፈፀመ ያለው ምን እንደነበር እንመልከት፡፡ 
ተፈፀመ-በእግዚአብሄር እና በሰው መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ አበቃለት
የሰውና የእግዚአብሄ ጠላትነት አበቃለት፡፡ አሁን ማንም ሰው ሃጢያተኛ እንደሆነ አምኖ በንስሃ ወደ እግዚአብሄር ከመጣ እግዚአብሄር በይቅርታ ይቀበለዋል፡፡
እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ኤፌሶን 2፡14-15
ተፈፀመ-እግዚአብሄርንና ሰውን የማስታረቅ ስራ ተጠናቀቀ
እግዚአብሄርና ሰው የተጣሉበት የሃጢያት እዳ ፈፅሞ በመከፈሉ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ይችላል፡፡ ሰው ካሁን በሁዋላ ከአግዚአብሄ ጋር ጠላት ሆኖ ቢኖር ስላልፈለገ እንጂ የሃጢያቱ እዳ ስላልተከፈለለት አይደለም፡፡ 
እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19
ተፈፀመ-አሮጌው ኪዳን
ሰዎች በስራ ከእግዚአብሄር ተቀባይነት የሚያገኙበት አሮጌው ኪዳን ተፈፀመ፡፡ አሁን ሰው የኢየሱስን የመስቀል ስራ ለእኔ ነው ብሎ በመቀበል ብቻ ይፀድቃል የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናል፡፡
ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና። ሮሜ 3፡28-29
ተፈፀመ-የሃጢያት እዳ ሁሉ ተከፈለ
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለውን የሃጢያት እዳ በእምነት መቀበል እንጂ ማንም ስለሃጢያት እዳው ለመክፈል መሞከር የለበትም፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #መስቀል #ስቅለት #ጠቦት #በግ #ደም  #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተፈፀመ #መስቀል #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment