የዚያን ጊዜም፦ ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን፤ ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት። እርሱም፦ እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ አላቸው። ዮናስ 1፡8-9
ነቢዩ ዮናስን ስራህ ምንድነው ብለው በጠየቁት ጊዜ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ ብሎ ነበር የመለሰው፡፡
እግዚአብሄርን ማምለክ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ቤተክርስትያን አዳራሽ መሄድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ መዘመር አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ሁለንተናችነን የሚጠይቅ መሰጠት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ 24 ሰአትና 7 ቀን የሚጠይቅ የህይወት ዘይቤ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ከንግግር ያለፈ ሙሉ አስተሳሰብንና ሙሉ ድርጊትን የሚጠይቅ መሰጠት ነው፡፡
እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት
1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ቅዱስ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሃያል አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረንና ህይወታችንን በእጁ የያዘ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከእግዚአብሄር ጋር በጥንቃቄ መኖር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን አለመናቅ ማክበር ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። ዘጸአት 20፡7
2. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና መስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን እንደ በላይ አምላክ ማየት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በምናደርገው በማንኛውም ነገር የእርሱን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርብን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄርን ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት ማለት ነው፡፡
ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ሮሜ 1፡20-21
3. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄር መገዛት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄር እሺ ማለት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን መስማትና መታዘዝ ማለት ነው፡፡
እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ያዕቆብ 4፡7
4. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት የእግዚአብሄር ባሪያ መሆን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት የራስን ፈቃድ ለእግዚአብሄር አሳልፎ መስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእኛ ደስታ ሳይሆን ለእሱ ደስታ መኖት ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን። ያዕቆብ 1፡1
5. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር መልካምነት መሳብ መደነቅ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር ባህሪ መማረክ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምልክ ማለት በእግዚአብሄር አሰራራ መዋጥ ማለት ነው፡፡
በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ራእይ 1፡16-17
በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ። እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። መዝሙር 66፡2-3
6. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ማፍቀር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሄርን መውደድ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከምንም በላይ ለእግዚአብሄር ያለንን ፍቅር ማስበለጥ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ሙሉ ትኩረታችንን ለእግዚአብሄር መስጠት ማለት ነው፡፡
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማርቆስ 12፡29-30
7. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር መታመን ማለት ነው፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ ምሳሌ 3፡5
8. በእግዚአብሄር ደስ መሰኘት ማለት ነው፡፡ አግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር መመካት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምልክ ማለት በእግዚአብሄር ከፍ ከፍ ማልት ነማለት ነው፡፡
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። መዝሙር 105፡3
9. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ብቻ ተስፋ ማድረግ ማለት ነው፡፡
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው። መዝሙር 39፡7
10. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሄርን መፈለግ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ምንንም ነገር ከእግዚአብሄር አለማስተካከል ማለት ነው፡፡
ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም። መዝሙር 34፡10
11. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ከሌሎች ነገሮች ለይቶ ማየት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ከሌሎች ነገሮች ጋር አለመቀላቀል ማለት ነው፡፡
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14-15
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ጌታ #አምላክ #ኢየሱስ #ቃል #መገዛት #አምልኮ #መስማት #መታዘዝ #መውደድ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መከተል #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ