ቢቻልህ
ግን እዘንልን እርዳንም አለው። ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23
ለሚያምን
ሁሉ ይቻላል፡፡
ሁሉ?
አዎ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡
ተመልከቱ
ለእኔ ለኢየሱስ ሁሉ ይቻላል አይደለም ያለው ኢየሱስ፡፡ ኢየሱስ ትሁት በመሆኑ ራሱን ከሁላችን ጋር አስተባብሮ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
ይላል፡፡
በእምነት
ውስጥ ያለው እምቅ ጉልበት ይህ ነው የሚባል አይደለም፡፡ካመንክ ለአንተ ሁሉ ይቻላል፡፡ ከአምንሽ ለአንቺ ሁሉ ይቻላል፡፡ ለሚያምን
ሁሉ ይቻላል፡፡
እግዚአብሄር
ሁሉን ቻይ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሁሉን ማድረግ ይችላል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለሚያምን እንዲሁ ሁሉ ይቻለዋል፡፡ ለሚያምን
ሁሉ ይቻላል፡፡
እምነት
የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአበሄርን ፈቃድ ከመረዳት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ
ለተረዳና እንደ ፈቃዱ ለሚኖር ሰው ሁሉ ይቻለዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ልብ ተረድቶ እንደ እግዚአብሄር ሃሳብ ለኖረ ሰው ሁሉ ይቻላል፡፡
በሚያምነውን ሰው አንደበት የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉን ማድረግ ይችላል፡፡ በሚያምነው ሰው ህይወት ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል ሁሉን
ማድረግ ይችላል፡፡
ለሚያምን
ሰው ሁሉን ቻዩ የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉን ይቻላል፡፡ ለሚያምን ሰው ሰማይና ምድርን የፈጠረውን የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉ ያስችለዋል፡፡
በእግዚአብሄን ቃል የሚደገፍ ሰው አይወድቅም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሊቋቋም የሚችል እንደሌለ የእግዚአብሄርን ቃል የሚያምነውን
ሰው ሊቋቋም የሚችል ሃይል ከሰማይ በታች የለም፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡
ለሚያምን
ሁሉ ይቻላል!
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment