Popular Posts

Thursday, March 9, 2017

ሰውን የማዳን ሃላፊነት የለብንም

ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20
በህይወታችን ያለው ስልጣን አላማ ወንጌልን እንድንሰብክት ነው፡፡ እውነተኛውን የክርስትና ሃይል የምንለማመደውም ወንጌልን ስንኖረውና ስንናገረው ነው፡፡
መንፈሳዊ ነገር የእግዚአብሄርና የሰው የጋራ ስራ ነው፡፡ የወንጌል ስራ የእግዚአብሄርና የሰው የአጋርነት ስራ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የማያደርገው ነገር አለ፡፡ ሰው የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ ሰው ደግሞ የማያደርገው ነገር አለ፡፡
የሰው ሃላፊነት ሌላውን ማዳን አይደለም፡፡ የሰው ሃላፊነት ወንጌሉን መናገር ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ሃላፊነት ደግሞ ወንጌሉን መስበክ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ሃላፊነት በተነገረው ወንጌል ተጠቅሞ ሰውን መውቀስ ነው፡፡
የጌታን ትእዛዝ የታዘዙትወጡና ወንጌልን ሰበኩ፡፡ እግዚአብሄርም ከእነርሱ ጋር በሃይል ይሰራ ነበር፡፡  
እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር። ማርቆስ 16፡15-16፣20
እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? ሮሜ 10፡14-15
ወንጌልን ለመስበክ ያለን እድል ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ወጥተን ወንጌልን እንናገር፡፡ 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment