Popular Posts

Monday, March 6, 2017

ብራብም ላንተ አልነግርህም ይላል እግዚአብሄር

የእግዚአብሄርና የህዝቡ ግንኙነትእንዲሳካ የሰው ዝንባሌ መስተካከል እንዳለበት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ክቡር ነው፡፡ እኛ ህዝቡ ከእግዚአብሄር ጋር ባለን ማንኛውም ግንኙነት ትክክለኛን ዝንባሌና ልብ ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡  እኛ ህዝቡ ከእግዚአብሄር ጋር ባለን አካሄድ እንደሚገባ መመላለስ አለብን፡፡
አንደኛው ዝንባሌ ለእግዚአብሄር የምናሳየው የምስጋናን አመለካከት ነው፡፡
እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የማይለወጥ መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ምንም እንከን የማይወጣለት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር የመልካምነት መጨረሻ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ መልካም ሆኖ ወደ እግዚአብሄር የምንቀርበው በመልካም ልብና በምስጋና ልብ ካልሆነ አግባብ አይሆንም፡፡
እግዚአብሄር ይህን ሁሉ አድርጎለት ወደእግዚአብሄር ሲቀርብ ካለምስጋና የሚቀርብ ሰው የተሳሳተ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር ምንም የማይወጣለት መልካም ሆኖ ወደእግዚአብሄር ሲቀርብ ማመስገን የማያውቅበት ሰው ያልገባው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው፡፡ እግዚአብሄር የመልካምነት ጣራው ሆኖ ሳለ እግዚአብሄርን ማመስገን ካላወቀ ተሸውዷል፡፡
እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር መስዋእት ሲያመጡ ካለምስጋና ያመጡለት ነበር፡፡ እስራኤላዊያን መስዋእት ሲያቀርቡ ምስጋናን ያልተሸከመ የእንስሳን መስዋእት ያመጡለት ነበር፡፡ እስራኤላዊያን ምስጋናን እንዲሸከም የተሰጣቸውን መስዋእት ካለ ምስጋና ባዶውን ወደ እግዚአብሄር ይሸኙት ነበር፡፡
እግዚአብሄርም ሲገስፃቸው እናያለን፡፡
ለእግዚአብሄር የምናደርገውን ነገር ሁሉ በምስጋና ካላደረግነው እግዚአብሄር አይቀበለውም፡፡ ለእግዚአብሄር የምንሰዋው መስዋእት ሁሉ ምስጋናን የሚሸከም መስዋእት መሆን አለበት፡፡ ለእግዚአብሄር የምናቀርበው ንግግር ሁሉ በምስጋና መሆን አለበት፡፡ ኑሮዋችን ሁሉ የእግዚአብሄርን ምስጋና የሚያሳይና የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት፡፡
በምስጋና ልብ ያልተደረገ ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ክብደት የለውም፡፡
ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፤ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ። ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው። ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፤ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው። ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙረ ዳዊት 50፡7-14፣23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ምስጋና #መዳን #እምነት #ሞት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment