ባለን በምንም ነገር ላይ ከመደገፍ በእግዚአብሄር መደገፍ ይሻላል፡፡ ያለን ምረጥ ነገር እንድንደገፍበት የሚያስችል አይደለም፡፡ ሰዎች የሚደገፉባቸው ነገሮች ሁሉ ሲያሳዝኑዋቸውና ሲክዷቸው ይታያል፡፡
1. በእግዚአብሄር እንድንደገፍ ታቅደን ስለተሰራን ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ሰላም ስለሌለ ነው፡፡
በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። ኢሳይያስ 26፡3
2. ምንም ልንደገፍበት የምንችል ነገር ስለሌለ ነው፡፡
በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ። ምሳሌ 11፡28
3. በሰው ወይም በሌላ ነገር መታመን ስለሚያዋርድ ነው፡፡
ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና። 2ኛ ዜና 32፡8
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። ኤርምያስ 17፡5-6
4. ካለእርሱ ምንም ልናደርግ ስለማንችል ነው፡፡
ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና ዮሃንስ 15፡5
5. በእግዚአብሄር መደገፍ ከምንም ባለጠግነት በላይ ባለጠግነትና ብሩክነት ስለሆነ ነው፡፡
የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው። መዝሙር 84፡12
6. በእግዚአብሄር የሚታመን ሰው መቼም ስለማይወድቅ ነው፡፡
የአለም ታሪክ ሁሉ የሚናገረው እግዚአብሄርን ታምኖ የተጣለ ሰው እንደሌለ ነው፡፡
ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። መዝሙር 9፡10
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ኢሳይያስ 40፡31
7. ውስንና በራሳችን ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች ስላሉ ነው፡፡
በህይወት ጎዳና ከመጀመሪያ መጨረሻውን ሁሉ ስለማናውቀው በእግዚአብሄር ላይ ታምነን ብቻ ነው እርምጃ የምንወስደው፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡28
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ ምሳሌ 3፡5
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መደገፍ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment