Popular Posts

Tuesday, March 14, 2017

አስተማሪ መሳጭ ታሪክ

አንድ አረጋዊ ባሕር ዳርቻ መንገድ ላይ እየሄደ እያለ አንድ ወጣት አጎንብሶ የሆነ ነገር በማንሳት ወደ ውቆያኖስ ውስጥ ሲጥል ከሩቅ ያየዋል፡፡
እየተጠጋ ሲሄድ እያነሳ ወደውሃ ውስጥ የሚመልሰው ኮከበ ባህር /ስታር ፊሽ/ መሆኑን ተገነዘበ፡፡
ይበልጥ ተጠግቶት ደህና አደርክ ብሎ ሰላምታ ከሰጠው በኋላ "ምን እያደረግክ ነው?" ሲል ጠየቀው፡፡  
ወጣቱ አዛውንቱን ለአፍታ ተመልክቶ "ኮከበ ባሕር ወደውቅያኖስ እየወረወርኩ ነው ይለዋል"፡፡
አዛውንቱ ፈገግ ብሎ ወጣቱን እንዲህ ሲል ጠየቀው "ለምንድነው ኮከበ ባሕሩን ወደውቅያኖስ ውስጥ የምትመልሰው ?"
ወጣቱም "ፀሐይ እየወጣ ነው ማእበሉ እየሰከነ ነውና መልሼ ውሃው ውስጥ ካልከተትኳቸው ይሞታሉ" አለው፡፡
አረጋዊውም ወጣቱን "በባሕሩ ዳርቻ ብዙ ምእራፍ ርቀት ላይ ብዙ ኮከበ ባህሮች አሉ፡፡ ያንተ እነዚህን ጥቂት ኮከበ ባህሮች ወደ ውሃው ውስጥ መመለስ ምን ልዩነት ሊያመጣ ይችላል?" ሲል ጠየቀው  
ወጣቱ ጎንበስ ብሎ አንዱን ኮከበ ባህር ወደውቂያኖሱ እየወረወረ "ለዚህ ለአንዱ ኮከበ ባሕር ልዩነት አመጣለሁ" አለው፡፡
አሁንም በምድራችን ያለውን የድህነት ችግር ለመፍታት ከሞከርን ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ በሁሉ ሰው ህይወት ልዩነት ማምጣት ላንችንል እንችላለን፡፡ መርዳት ለምንችለው ለአንዱ ግን ልዩነት እናመጣለን፡፡ የአንዱን ኑሮ ግን መለወጥ እንችላለን፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #መስጠት #ድሃ #ምፅዋት #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

1 comment: