Popular Posts

Wednesday, March 22, 2017

የብዙ ጥያቄ መልስ

ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው። ምሳሌ 16፡16
ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና። ምሳሌ 3፡14
በህይወት የብዙ ጥያቄያችንን መልስ የምንፈልገው በተሳተ ቦታ ነው፡፡ በተለይ ወርቅና ብር ውስጥ የህይወት ጥያቄያችን ሁሉ መልስ ያለ ይመስለናል፡፡ ተጨማሪ ገንዘብ ባገኝ የህይወት ጥያቄዬ ይመለሳል ብለን እናስባለን፡፡ ለምሳሌ በህይወት ያሉብንን ተግዳሮቶች ለማለፍ ብዙ ጊዜ የሚያስፈልገን ቁልፍ ተጨማሪ ገንዘብ ሳይሆን ተጨማሪ ጥበብ ነው፡፡
ጥበብ ያለንን ነገር እንዴት በሚገባ እንደምንጠቀምበት ያስተምረናል፡፡ ጥበብ ምን ማደርግ እንዳለብን በማናውቅ ጊዜና ህይወት ፈተና ሲሆንብን ምን ማድረግ እንዳለብን መንገዱን ያሳየናል፡፡ ስለዚያ ነው በፈተና የሚያልፍ ሰው ጥበብ ይለምን እንጂ ይበለጥ ገንዘብ ይለምን የማይለው፡፡ በጥበብ የማይፈታ ችግር የማናልፈው ፈተና የለም፡፡ በእግዚአብሄር ጥበብ በእግዚአብሄር እይታ ካየነው ሊፈታ የማይቻል ነገር የለም፡፡  
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡2-5
እኩል ገንዘብ ያላቸውን ሁለት ሰዎች የሚለየው ጥበባቸው ነው፡፡ አንዱ እንዴት በጥበብ እንደሚያስተዳድርው ያውቃል ሌላው ደግሞ ጥበብ ይጎድለዋል፡፡ ሰው ደግሞ ምንም ነገር ቢኖረው እንዴት እንደሚያስተዳድረው ጥበቡ ከሌለው እንደሌለው ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ከሃብት ሁሉ በላይ ማስተዋልን እንድናተርፍ የሚያስተምረን፡፡
ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልን አግኝ፤ አትርሳም፥ ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል። አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች። ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ምሳሌ 4፡5-7
ጥበብ የሚገኘው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ በእምነት ወደፈእግዚአብሄር በመፀለይ ጥበብን እንቀበላለን፡፡
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡5
ሌላው ጥበብ የሚገኘው በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መረዳት ጥበበኛ ያደርጋል፡፡
ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።  2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment