ያለ
እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
እግዚአብሄር
በተፈጥሮ አይናችን የማይታይ መንፈስ ነው፡፡ የእግዚአብሄርም መንግስት እንዲሁ በአይን የማይታይ መንፈስ ነው፡፡
ከእግዚአብሄር
ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግ የሚፈልግ ሰው ማድረግ የሚችለው በእምነት ነው፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን ማየት አይቻልም፡፡
ካለ እምነት እግዚአብሄርን ማግኘት አይቻልም፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን መድረስ አይቻልም፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን መንካት
አይቻልም፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር መቀበል በፍፁም አይቻልም፡፡
ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ሰው በመጀመሪያ እግዚአብሄር
እንዳለ ማመን አለበት፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው ከእግዚአብሄር ሊቀበል በፍፁም አይችልም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው ከእግዚአብሄር የሚቀበልበት ሁኔታ ላይ
ሊገኝ አይችልም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው እግዚአብሄርን ሊነካው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው የእምነት
እጆቹን ዘርግቶ ከእግዚአብሄር መቀበል ይሳነዋል፡፡
ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ሰው እግዚአብሄር በትጋት
ለሚፈልጉት ዋጋ እንደሚሰጥ ሊያምን ይገባዋል፡፡ ወደእግዚአብሄር የሚመጣ እግዚአብሄር ቸርና ርህሩህ በመሆኑ ብቻ ለሚፈልጉት ዋጋ
እንደሚሰጥ ያመነ ዘንድ ይገባዋል፡፡ እግዚአብሄር ለሚፈልጉት ዋጋን የሚሰጥ ልዩ ከፋይ እንደሆነ ሊያምን ይገባል፡፡ ወደእግዚአብሄ
የሚደርስ እግዚአብሄርን መፈለግ እጅግ አትራፊ ስራ እንደሆነ ሊረዳ ያስፈልገዋል፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ ጥበበኛ ኢንቨስትመንት
እንደሆነ ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚደርሰው ሰው እግዚአብሄርን በመፈለግ ላይ ጊዜንና ጉልበትን ማፍሰስ እጅግ አትራፊ
ስራ መሆኑን ሊረዳ ይገባዋል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር
የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment