እግዚአብሄር
ሰውን የፈጠረው ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት በማድርግ እግዚአብሄርን በምድር ላይ እንዲወክለው ነው፡፡ እግዚአብሄር የዘላለም
ንጉስ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን እንዲታዘዝ ነው፡፡ የእግዚአብሄርና የህዝቡ የአምላክና የህዝብነት ግንኙነት ደረጃ የሚወሰነው
ህዝቡ ቃሉን ሰምቶ በማድረጉ ላይ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን በሁሉ ለመታዘዝ ነው፡፡ የእግዚአብሄርና የሰው ግንኙነት
የሚሰምረው ሰው እንደፍጥረቱ እግዚአብሄርን ሲታዘዝ ብቻ ነው፡፡
አልሁም፦
ቃሌን ስሙ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ። ኤርምያስ 11፡4
ሰው
የእግዚአብሄርን አምላክነት ጥቅም ሁሉ የሚያጣጥመው እግዚአብሄርን ሲሰማውና ሲታዘዘው ብቻ ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ጥላ የሚያገኘው
ሲታዘዘው ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ሃይል የሚለማመደው እግዚአብሄር በሚፈልገው መንገድ ሲሄድ
ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ሃይልና እውቀት ሙሉ ተጠቃሚ የሚሆነው እግዚአብሄርን በቃሉ ሲታዘዘው ብቻ ነው፡፡
እንግዲህ
ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡19-20
ሰው
በእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ክብር የወደቀው እግዚአብሄርን መታዘዝ ሲያቆም ነው፡፡ የሰው ክብር እግዚአብሄርን
መታዘዙ ነው፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakum...
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መታዘዝ #መስማት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #መውደድ #መስጠት #መልካምነት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment