Popular Posts

Sunday, March 5, 2017

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ

ኢየሱስ በምድር ላይ ሲያስተምር በጣም አስፈላጊና ከበድም ስላሉ ነገሮች ሲናገር የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ይል ነበር፡፡ እግዚአብሄርን ያሳወቀን ኢየሱስ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ልዕብ የገለጠልን ኢየሱስ ነው፡፡ ኢየሱስ ጆሮ ያለው ይስማ ሲል በእርግጥ ጆሮ ያለው ሁሉ ሊሰማው ሊያስተውለውና ሊድንበት የሚገባ ነገር ነው፡፡
መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው። ዮሃንስ 1፡18
·         የእግዚአብሄርን ቃል አሰማማችን ለፍሬያማነታችን ወሳኝ ነው - የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ
በምሳሌም ብዙ ያስተምራቸው ነበር፥ በትምህርቱም አላቸው፦ ስሙ፦ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት። ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም። ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ አለ።የማርቆስ ወንጌል 4:3-9
·         እግዚአብሄር ሁሉን ያያል ወደ ብርሃንም ያመጣዋል - የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ
እንዲህም አላቸው፦ መብራትን ከዕንቅብ ወይስ ከአልጋ በታች ሊያኖሩት ያመጡታልን? በመቅረዝ ላይ ሊያኖሩት አይደለምን? እንዲገለጥ ባይሆን የተሰወረ የለምና፤ ወደ ግልጥ እንዲመጣ እንጂ የተሸሸገ የለም። የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። ማርቆስ 4:21-23
·         የእኛ ክብራችን ጌታን መከተልና የምድር ጨው መሆን ነው፡፡ ከጌታ ህይወት ውጭ ህይወታችን ትርጉም የለውም - የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ
እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፈጣል? ለምድር ቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባም፤ ወደ ውጭ ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ሉቃስ 14፡33-35
·         ክርስትና ተጋድሎ ነው፡፡ ተጋድለን ድል ከነሳን ብቻ ነው ከእጊአብሄር ሽልማትን የምንቀበለው- የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ። ራእይ 2፡7
·         ለህዝብ ሁሉ ምስክር ይሆን ዘንድ ወንጌል በአለም ሁሉ ይሰበካል - የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል። እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥  ማቴዎስ ወንጌል 24፡14-15
·         መጀመር ብቻ ሳይሆን እስከመጨረሻ መፅናት ይጠበቅብናል - የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ
ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ። ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤ የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ። መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ራእይ 2፡25-29
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ጆሮያለውይስማ #ቃል #እግዚአብሄር #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ማስተዋል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment