እግዚአብሔር
መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። ናሆም 1፡7
ማስታዋሉ የማይመረመር የምድር ዳርቻ ፈጣሪ መልካም
ባይሆን እንዴት እንሆን ነበር? ሁሉን ያደርግ ዘንድ ቻይ የሆነ እግዚአብሄር መልካም ባይሆን ምን እንሆን እንደነበር ማሰብ ይከብዳል፡፡
እግዚአብሄር ለመረዳት የሚያዳግተውን ሃይሉን የሚጠቀመው
በመልካምነት ነው፡፡ እግዚአብሄር የማይመረመረውን ማስተዋሉንና ጥበቡን የሚጠቀመው በመልካምነት ነው፡፡
የእግዚአብሄር መልካምነት የማይለዋወጥ ቋሚ ነው፡፡
አንድ ቀን ይለወጥ ብለን የምንፈራው አይደለም፡፡
እኔ
እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም። ሚልክያስ 3፡6
እግዚአብሄር
ሁለንተናው መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄርን በግራም በቀኝም ብታዩት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያዕቆብ 1፡16-17
እግዚአብሄር መልካም ብቻ ሳይሆን የመልካምነትም
ጣራው ነው፡፡ ስለ መልካምነት ክርክር ቢነሳ ሊፈታው የሚችል እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም ያለው መልካም ነው እግዚአብሄር
መልካም ያላለው መልካም አይደለም፡፡
ስለዚህ ነው ሁል ጊዜ በነገር ሁሉ እግዚአብሄርን
ማመሰገን መልካም የሆነው፡፡ እግዚአብሄር ሁለንተናው መልካም ስለሆነ እግዚአብሄን ማመስገን መልካም ነው፡፡ ሰው ሌላ ነገር አድርጎ
ቢስት እግዚአብሄርን በማመስገኑ የሚሳሳት ሰው የለም፡፡
እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። መዝሙር 92፡1፣4
በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡18
እግዚአብሔር
ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፡፡ መዝሙር 135፡3
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች
ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ
#መልካም #እምነት
#ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ሰላም #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #የዘላለምህይወት
#ቸር #መንፈስ
#መንፈስቅዱስ
No comments:
Post a Comment