Popular Posts

Follow by Email

Thursday, March 23, 2017

ታላቅ ሚስጥር

ክርስትና ከባዶ ከሃይማኖቶች አንዱ አይደለም፡፡ ክርስትና የእግዚአብሄርና የሰው እውነተኛ ግንኙነት ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሄርና የሰው ግንኙነት ሃሳባዊ ግንኙነት ሳይሆን የተግባርና የእለት ተእለት ግንኙነት ነው፡፡
ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች ልዩ የሚያደርገው ክርስቶስ በተከታዮች ውስጥ መኖሩ ነው፡፡ ክርስቶስ በተከታዩ ልብ ውስጥ በመንፈሱ ይኖራል፡፡  
በክርስትና ህይወታችን በስኬታማነት ለመኖር ክርስቶስ በልባችን እንደሚኖር ማመን አለብን፡፡ ክርስትናን ብቻችንን አንኖረውም፡፡ ክርስትናን በራስ እውቀትና በራስ ሃይል የሚኖር አይደለም፡፡ ክርስቶስ ሁልጊዜ ሊመራን በልባችን እንዳለ ማወቅ አለብን፡፡
ራሳችንን በውስጣችን ላለው ክርስቶስ እንዲመራን ከሰጠን እግዚአብሄር ወደ አየልን ግብ የማንደርስበት ምንም ምክኒያት አይኖርም፡፡  
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ገላትያ 2፡20
ክርስቶስ ሃይል ሊሆነን በልባችን እንዳለ ልንረዳ ይገባናል፡፡ ክርስትናን በሙላት ለመኖር ክርስቶስ በእኛ እንደሚያድር ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡
ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው። ሮሜ 8፡10
ክርስቶስ በውስጣችን እንዳለ ማመን ፣ ማወቅ ፣ መረዳትና ለምሪቱ ንቁ መሆን አንዳለብን መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡   
በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ ኤፌሶን 3፡16-17
በምድር ላይ በስጋ ሲመላለስ አሸናፊ የነበረው ክርስቶስ አሁን እኛንም አሸናፊዎች ሊያደርገን  በመንፈስ በእኛ ውስጥ መኖሩ እጅግ ታላቅ ሚስጥር ነው፡፡
ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል፤ ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። ቆላስይስ 1፡26-27
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #የእግዚአብሄርቤተመቅደስ #ክርስቶስ #ክርስቶስበእኛ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በመንፈሱ #የእግዚአብሄርቤተመቅደስ #እምነት

No comments:

Post a Comment