መፅሃፍ ቅዱስ በምድር ላይ ስለኖሩና ስለሞቱ ሰዎች
በግልፅ ይናገራል፡፡ በምድር ላይ የኖሩ ሰዎች ከሞቱ በኋላ በምድር ላይ ምንም እድል ፈንታ እንደሌላቸው መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ ያስተምራል፡፡
ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም። ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም። መጽሐፈ መክብብ 9፡5-6
ሰው
ሲሞት የቀብር ስነ ስርአት የሚደረግለት ስለዚህ ነው፡፡ ወንድና ሴት ለመጋባት ሲወስኑ የሚያውቋቸውን ዘመድ እና ወዳጆቻቸውን አብረዋቸው
ደስ እንዲላቸውና ምስክር እንዲሆኑ ይጠራሉ፡፡ በጋብቻ ስርአት የሚጋቡት ሴትና ወንድ ከዚህ በኋላ እርሷም የማንም ወንድ ልትሆን
እንደማትችል እርሱም ከዚህ በኋላ የማንም ሴት ሊሆን እንደማይችል በግልፅ ለህዝብ ሁሉ ያውጃሉ፡፡ በዚያ ቦታ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ
ይህች ሴት የዚህ ወንድ ብቻ ይህ ወንድ የዚህች ሴት ብቻ እንደሆኑ ያውቃል፡፡
በተመሳሳይ
መልኩ ሰው ሲሞት ከተቀበረ በኋላ ይህ ሰው በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት እድል ፈንታ እንደሌለው የሚታወጅበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ
ሰው ሲቀበር ያየ ሰው ሁሉ መለየቱን ከዚህ ከሞተ ሰው ጋር ከዚህ በኋላ ምንም አይነት ግንኙነት እንደማይደረግ ያውጃል፡፡ በምድር
ሲኖር ምንም ፃዲቅና ቅዱስ ሰው ቢሆን ከሞተ በኋላ ግን የዚያን ሰው መንፈስ ማናገር ራስን ለአጋንንት መንፈስ ማጋለጥ ነው፡፡
ከሞቱ
ሰዎች ጋር የምናደርገው ማንኛውም ግንኙነት አደገኛ ነው፡፡ የሞቱ ሰዎችን ማናገር ወይም ሙታንን መሳብ በመፅሃፍ ቅዱስ የተወገዘ
ድርጊት ው፡፡
አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ኦሪት ዘዳግም 18፡11
የቅድመ አያት ፣ የአያት ፣ አባቶች መንፈስ ይሁን
ሌላ የሞተ ሰው መንፈስ በህያዋን ህይወት ላይ ምንም እድል ፈንታ የለውም፡፡
ሳኦል በጨነቀው ጊዜ የሞተውን የሳሙኤልን ሙት መንፈስ እንደጠራና እግዚአብሄርን
እንዳስቆጣው መፅሃፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 28፡7-15
በአለም ላይ ሁለት አይነት መንፈሶች አሉ፡፡ በአለም ላይ የእግዚአብሄር የሆነ ቅዱስ
መንፈስ አለ በአለም ላይ እንዲሁ የሰይጣን የሆነ ክፉ መንፈስ አለ፡፡
ሰው የሞተና የተቀበረን ሰው መንፈስ በሚጠራ ጊዜ እርኩስ መንፈስ ሊገናኘው ስለሚችል
ነው መፅሃፍ ቅዱስ ሙት መንፈስን መጥራትን እንደሌለብን የሚዘው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ የከለከለውን የሞተን ሰው መንፈስ የሚጠሩ
ሰዎች ራሳቸውን ለክፉ መንፈስ ያጋልጣሉ፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሔርመንፈስ #እርኩስመንፈስ #ሰይጣን #ፈትኑ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነቢያት #ነቢይ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment