Popular Posts

Thursday, December 6, 2018

ለሚያምን ይቻላል


ሰው ወይ ራሱ መቻል አለበት ወይም ደግሞ በሚችለው መታመን አለበት፡፡ ራሱ የማይችለው ወይም በሚችለውም የማይታመን ሰው ይወድቃል፡፡
እግዚአብሄር ሁሉን ይችላል፡፡
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሄር የሚታመን ሰው ሁሉን በሚያስችለው በእግዚአብሄር ሃይል ይበረታል፡፡ ሁሉን በሚችለው በሚታመን ደግሞ እንዲሁ ሁሉን ይችላል፡፡
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል፥ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16፡9
እግዚአብሄር ማድረግ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ሁሉ የሚሳነው በሌለ በእግዚአብሄር ሃይል የሚታመን ሰው እንዲሁ በእግዚአብሄር ሃይል የሚሳነው ነገር አይኖርም፡፡  
እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን? ትንቢተ ኤርምያስ 32፡27
ለእግዚአብሄር ሁሉ ቀላል እንደሆነ ሁሉ ቀላል በሆነለት በእግዚአብሄር ለሚታመን ሰው ሁሉ ቀላል ነው፡፡
በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች። ኦሪት ዘፍጥረት 18፡14
የእግዚአብሄርን ሃሳብ ሊከለክል የሚችል ሰው እንደሌለ መጠን እንዲሁ በእግዚአብሄር በሚታመን ሰው የሚፈፀመውን የእግዚአብሄርን ሃሳብ ሊከለክል የሚችል ምንም ሃይል የለም፡፡
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። መጽሐፈ ኢዮብ 42፡2
ጥበብና ማስተዋሉ የማይመረመር እግዚአብሄር ሁሉን ማድረግ እንደሚችል ሁሉ በእግዚአብሄር ጥበብና ማስተዋል የሚታመን ሰው ሁሉን በሚችል አምላክ ጥበብ ይወጣል በጥበብ መፍታት የሚያቅተው ነገር አይኖርም፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡28
ሁሉም በሚቻለው በእግዚአብሄር የሚያምን ሰው ሁሉን በሚቻለው በእግዚአብሄር ሃይል ይኖራል ይወጣል ይገባል፡፡
ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። የማርቆስ ወንጌል 9:23
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment