Popular Posts

Follow by Email

Saturday, December 1, 2018

የምላስ የሞትና የሕይወት እጅ


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 18፡21
አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወዷትም ፍሬዋን ይበላሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 18፡21 /አዲሱ መደበኛ ትርጉም/
ምላስ ትልቅ ሃይል ያለው የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ንግግር ታላቅ የታመቀ ሃይል አለው፡፡ አንደበት በተሳሳተ ሁኔታ ከተጠቀምበት ሊያፈርስ የሚችል በትክክለኛ መንገድ ከተጠቀምንበት ደግሞ ሊገነባ ሊያነፅ የሚችል ታላቅ ጉልበት አለው፡፡
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡29
ንግግር ክፉም ለማድረግ መልካምም ለማድረግ ታላቅ ብቃት አለው፡፡
በአንደበታቸው ላይ ያለውን ታላቅ ሃይል በትክክል የሚረዱና ለትክክለኛው ነገር የሚጠቀሙበት ሰዎች ፍሬያማ ይሆናሉ፡፡ አንደበታቸውን በጥንቃቄ የሚይዙ ሰዎች በህይወት ፍሬያማ ይሆናሉ፡፡  
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #አንደበት #ምላስ #አፍ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፀጋ #እሳት #መልካምቀኖች #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment