Popular Posts

Sunday, December 9, 2018

ፍቅር ወይስ ፍርሃት


ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18
ፍቅርና ፍርሃት አብረው አይሄዱም፡፡
ፍርሃት ህይወታችንን እንዲመራው ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ ፍርሃት መጥፎ መሪ ነው፡፡ ፍርሃት የሚያስት መሪ ነው፡፡ ፍርሃት ማንንም በትክክል መርቶ አያውቅም፡፡ ፍርሃት ከመንገድ የሚያስወጣ መጥፎ መሪ ነው፡፡
ፍቅር መልካም መሪ ነው፡፡ ፍቅር መርቶት የተሳሳተ ሰው ፈፅሞ  አይገኝም፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ፍቅርን ተከታተሉ የሚለን ፍቅርን ተከትሎ ያፈረ ሰው በምድር ላይ ስለሌለ ነው፡፡ ፍቅርን ተከትሎ የተሳሳተ ሰው የለም፡፡ ፍቅርን ተከትሎ ከግቡ ሳይደርስ በመንገድ ላይ የቀረ ሰው የለም፡፡
ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡1
ፍርሃት የሰውን ፈቃድ አያከብርም፡፡ ፍርሃት ያጣድፋል፡፡ ፍርሃት ያስጨንቃል፡፡ ፍርሃት ሰውን ካለፈቃዱ ያስገድዳል፡፡ ፍርሃት የሰውን ነፃነት አያከብርም፡፡ ፍርሃት የሰውን ነፃ ፍቃድ ይጋፋል፡፡
ፍርሃት ይህን ካላደርግክ ይህ ይሆንብሃል ብሎ ያስፈራራል፡፡ ፍርሃት ሰውን ለድርጊት የሚያነሳሳው እና የሚያስገድድው በማስፈራራት ነው፡፡ ፍርሃት ክፉ ነጂ ነው፡፡ ፍርሃት እውቀትን ሰጥቶ ራስህ እንድትወስን ጊዜን እና እድልን አይሰጥም፡፡ ፍርሃት ወደ ጨለማ ሲገፈትር ፍቅር ወደ ብርሃን ይመራል፡፡  
ፍቅር ጨዋ ነው፡፡ ፍቅር እውቀትን ሰጥቶ መልካሙን ነገር እንድታደርገው ይመክራል እንጂ አያስገድድም፡፡
በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ ኦሪት ዘዳግም 30፡19
ፍቅር የአንተን እርምጃ ያከብራል፡፡ ፍቅር የአንተን እርምጃ ጥሶ ወደውሳኔ አያስቸኩልህም፡፡ ፍቅር ይጠብቃል፡፡ ፍቅር ራስ ወዳድ  ስላይደለ ይታገሳል፡፡
ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡7
ሰው የሚያደርገውውን ነገር በፍቅር ነው በፍርሃት ብሎ ራስን ማየት አለበት፡፡ ሰው የሚያደርገውን ነገር የሚያደርገው በፍርሃት ከሆነ በእስራት ውስጥ ነው ያለው፡፡ ሰው የሚያደርገውን የሚያደርገው በፍቅር ከሆነ በነፃነት ውስጥ ነው ያለው፡፡
በፍርሃት የምታደርገው ነገር ካለ በእስራት ውስጥ ነህ፡፡ በፍርሃት የምትወስነውን እያንዳንዱን ውሳኔ በፍቅር አልወሰንከውም ማለት ነው፡፡   
የሚፈራ ሰው ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡ ሰው በፍቅር የሚወስነው ውሳኔ ከፍርሃት የነፃ ነው፡፡ ፈፁም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥለዋል፡፡ የሚፈራ ሰው ውሳኔ ንፁህ ሊሆ አይችልም፡፡ በፍርሃት የተወሰነ ውሳኔ ችግር ሳይገኝበት አይቀርም፡፡
ፍቅር ሲወርሰን ፍርሃት ለቅቆን ይሄዳል፡፡ የፍቅር ጥራቱ የሚለካው ካለምንም ፍርሃት በመሆኑ ነው፡፡ ፍርሃት የተቀላለቀለበት ፍቅር የሚጎድለው ነገር አለ ሙሉም አይደለም፡፡ በፍርሃት የሚር ሰው ደግሞ በፍቅር ሊኖር ያቅተዋል፡፡ በፍቅር የሚኖር ሰው ካለፍርሃት ይኖራል፡፡
ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፍርሃት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

No comments:

Post a Comment