Popular Posts

Monday, December 10, 2018

0% ጭንቀት

ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6
ጌታ በግልፅ አታድርጉ ብሎ በመፅሃፍ ቅዱስ ካዘዛቸው ትእዛዛት አንዱ ጭንቀት ነው፡፡ ሰዎች ደግሞ በየእለቱ የሚፈተኑት በጭንቀት ነው፡፡
እግዚአብሄር ስለምንም እንድንጨነቅ አይፈልግም፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ያልተረዱ ሰዎች ካልተጨነቁ ስራ ይሰሩ አይመስላቸውም፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ የማየረዱ ሰዎች አለመጨነቅ እንደሚቻል እንኳን አያውቁም፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ የማያውቁ ሰዎች ሳይጨነቁ መኖር እንደማይችሉ አያውቁም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ዋና ዋና ነገር ላይ ብቻ እንድንጨነቀ እንደተፈቀደለን ያስባሉ፡፡ መጽፅሃፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ግልፅ ነው፡፡ በአንዳች አትጨነቁ በማለት የጭንቀት ቁራጭ በህይወታቸን ተቀባይነት እንደሌለው ያስተምረናል፡፡ በህይወታችን 1% ጭንቀርት አይፈቀድም፡፡ በህይወታችን የሚፈቀደው 0% ጭንቀት ነው፡፡ ህይወታችን ከማንኛውም አይነት የጭንቀት አይነቶች የፀዳ መሆን አለበት፡፡  
ሰው በምንም ሳይጨነቅ መኖር ይችላል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ያዘዘን ሁሉ የሚቻል ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር የማይቻል ነገርን አድርጉ ብሎ አያዝም፡፡ ምፅሃፍ ቀዱስ አትይጨነቁ የሚለው ሳይጨነቁ መኖር ስለሚቻል ነው፡፡ እንዲያውም ሰው በህይወቱ ፍሬያማ የሚሆነው በማይጨነቅበት መጠን ብቻ ነው፡፡ ፍሬያማነትና ጭንቀት ተቃራኒ ነገሮች ናቸው፡፡ ለጭንቀት  ከፈቀድንለት ፍሬያማነት ከህይወታችን ይለያል፡፡ ፍሬያማነት በህይወታችን ካለ ደግሞ ለጭንቀት አልፈቀድንለትም ማለት ነው፡፡
ነገር ግን ለምንድነው መፅሃፍ ቅዱስ ጭንቀትን በብዙ ቦታዎች የሚከለክለው ብለን መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡ ጭንቀት የሚከለከልበት ብዙ ምክኒያቶች አሉት፡፡
በህይወታችን አንድንም ጭንቀት ማስተደናገድ የሌለብን አምስቱ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ምክኒያች እንመልከት
1.      ጭንቀት ምክኒያታዊ ስላይደለ ነው
የሚያስበለት አባቱ እያለ የ 2 አመት ልጅ በሚመጣው ሳምንት ምን እበላለሁ ብሎ ቁጭ ብሎ ቢጨነቅ ምክኒያታዊ ያልሆነ ድርጊት ነው፡፡ ሁሉ የሚያውቅ ሁሉን የሚችል እግዚአብሄር አባታችን ሆኖ መጨነቅ ኢ-ምክኒያታዊ ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11
ሰው ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ያለ እግዚአብሄር አባቱ ሆኖ ከተጨነቀ ከዚያ በላይ የሚመጣለት ነገር አይኖርም፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 6፡30
እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
2.     ጭንቀት ፍሬ ቢስ ስለሆነ ነው
ጭንቀት ትጋት እና ስራ ይመስላል፡፡ ነገር ግን እንደጭንቀት ፍሬ ቢስ የሆነ ነገር በምድር ላይ የለም፡፡ ጭንቀት ስራ የሰራን እያስመሰለ በከንቱ ያፀናናናል፡፡ ካልተጨነቅን ሰነፍ የሆንን ሊመስለን እና ካለተጨነቅን ልንኮነን እንችላለን፡፡ ነገር ግን ጭንቀት 100% ፍሬ ቢስ ነገር ነው፡፡
ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? የማቴዎስ ወንጌል 6፡27
3.     ጭንቀት ቃሉን እንዳንታዘዝ ስለሚያግደን እንቅፋት ነው
ጭንቀት የማንችለውን ነገር በመሞከር የምንችለውን ነገር እንዳናደርግ የሚያግደን ክፉ እንቅፋት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሚሰራ የሚለውጥ ቢሆንም በሚጨነቅ ሰው ህይወት ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል መስራት አይችልም፡፡ ጭንቀት የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን ፈሬ እንዳያፈራ የሚያንቅ በሽታ ነው፡፡
በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። የሉቃስ ወንጌል 8፡14
4.     ጭንቀት ሁኔታዎችን ማምለክ ነው
ኢየሱስ ጭንቀትን ያገናኘው ገንዘብን ከመውደድ ጋር ነው፡፡ ጭንቀትና ገንዘብን መውደድ ሁለት የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ጭንቀትና ገንዘብን መውደድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ ገንዘብን መውደድ ደግሞ የክፋት ሁሉ ስር ነው፡፡  
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? የማቴዎስ ወንጌል 6፡24-25
5.     ጭንቀት ትእቢት ነው
እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን ነገር ማድረግ ትህትና ሳይሆን ትእቢት ነው፡፡ እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን ነገር ማድረግ አለመታዘዝና አመፃ ነው፡፡
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡7
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #ማረፍ #ፀጋ #ፀሎት #ልመና #ምስጋና #ምናን ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment