Popular Posts

Tuesday, December 4, 2018

የባለጠግነት ዋናው መመዘኛ


የባለጠግነት ዋናው መመዘኛ ብዙ ገንዘብ ማከማቸት አይደለም፡፡ የባለጠግነት ዋናው መመዘኛ መሰረታዊ ፍሎጎትን አሟልቶ ጌታን መከተል ነው፡፡
ጌታን ከመከተል በላይ ባለጠግነት የለም፡፡ የተፈጠሩበትን አላማ ከማገኘት በላይ ባለጠግነት የለም፡፡ ከፈጠረን ከእግዚአብሄር ጋር ከመታረቅ በላይ ባለጠግነት የለም፡፡ የተፈጠርንበትን የህይወት አላማ እግዚአብሄርን ከማምለክ በላይ ባለጠግነት የለም፡፡
ማንም ሰው ከመሰረታዊ ፍላጎቱ የተረፈ ገንዘብ ቢኖረው ሌሎችን ለመጥቀምና ለመርዳት ነው፡፡ ሰው ከመሰረታዊ ፍላጎት በላይ ተረፍ ያለ ሃብት ቢኖረው ሰዎችን በስሩ ቀጥሮ ለማሰራትና መሰረታዊ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉበትን የስራ እድል ለመፍጠር ነው፡፡ ሰው ከመሰረታዊ ፍላጎቱ ያለፈ ገንዘብ ቢኖረው ለሌሎች ጥላ ለመሆን ነው፡፡
ማንም ሰው ከመሰረታዊ ፍላጎት በላይ የተፈረ ሃብት ቢኖረው እንደ ባለ አደራ ለሌላው እንዲሰጥና እንዲያካፍል ነው፡፡
ሰው ብዙ ገንዘብ ስላለው ከአንድ ሰሃን በላይ ምግብ አይበላም፡፡ ሰው ብዙ ቤቶች ስላለው በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ቤቶች ውስጥ አይኖርም፡፡ ሰው ምንም ሃብታም ቢሆን ሁለት አልጋ ላይ አይተኛም፡፡
ሰው ተሳካለት ተከናወነለት የሚባለው መሰረታዊ ፍላጎቱን አማልቶ ጌታን ሲከተል ብቻ ነው፡፡ የሚቀናበት ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን የሚከተል ሰው ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment