Popular Posts

Friday, September 2, 2016

ስልጣኑ በእጃችን ነው !

ሰው ሲፈጠር ፈቃድ ያለው ተደርጎ ስለተፈጠረ አንድን ነገር ከማድረጉ በፊት ያስባል ምን ማድረግ እንዳለበትም ይወስናል፡፡ አስቦ የወሰነ ሰው የሚያደርገው እንዳሰበው እንደዚያው ነው፡፡
በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ . . . ምሳሌ 23፡7
ስለዚህ ነው ሁልጊዜ ስለመስረቅ የሚያስብ ሰው ሌባ ነው፡፡ ስለ ጥላቻ የሚያስብ ሰው የመውደድ አቅም ሊኖረው አይችልም፡፡
ሰው እርምጃውን ማስተካካል የሚችለው በሃሳብ ደረጃ ነው፡፡ ሰው በሃሳብ ደረጃ ብቻ ነው ምን ማድረግ እንዳለበት ሊወስን የሚችለው፡፡ ሰው ግን ሃሳቡን ሳይቆጣጠር ወደ አእምሮው የሚመጣውን ክፉ ሃሳብ ሁሉ እያሰበ መልካም ሰው እሆናለሁ ብሎ መጠበቀ እንክርዳድ ዘርቶ ስንዴን ለማጨድ እንደ መጠበቅ ነው፡፡ ሰይጣን ሰውን እጁን ጠምዝዞ በግድ ሃጢያትን ማሰራት አይችልም፡፡
ሰይጣን ሰውን ሃጢያት ሊያሰራ ሲመጣ የሚልከው ሃሳብን ነው፡፡ ሰው ሃሳቡን ከተቀበለውና ካስተናገደው ለመፈፀም የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡
ሃሳቡን ግን በፍጥነት ከተቃወምነውና ከጣልነው ክፋት ላለመስራት አቅም ይኖረናል፡፡ ሃሳባችንን ካልተጠቀመ በስተቀር ሰይጣን ሃጢያት ሊያሰራን በፍፁም አይችልም፡፡
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3
ምን ማሰብ እንዳለብንና እንደሌለብን የምንወስነው እኛ ነን፡፡ በማንኛውም ጊዜ ሃሳብ ሊመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሃሳቡን ለማስተናገድም ሆነ ለመጣል ስልጣኑ በእኛ እጅ ነው፡፡ ሃሳቡን ካላስተናገድነው በእኛ ላይ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ህይወታችንን በንፅህና ለመጠበቅና ለእግዚአብሄር የምንጠቅም ለመሆን የእግዚአብሄርን ቃል በተለይም እነዚህን አስቡ ተብሎ የተነገረውን ብቻ ማሰብ ያለብን፡፡
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8 ይህን ፅሁፍ
ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum...

No comments:

Post a Comment