ከእኛ በፊት ትውልድ ነበረ ፡፡ ከእኛም በኋላ ትውልድ ይመጣል፡፡ አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ስኬትም ሆነ ውድቀት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
በትውልዳችን እንዴት መኖር እንዳለብን ካወቅን በኋላ የምናስበው ስለሚመጣው ትውልድ ነው፡፡ እኛ ደስ ብሎን የተገዛንለት ጌታ ዘራችንም እንዲገዛለት ጥማታችን ነው፡፡ ለሚመጣው ትውልድ ለጌታ እንዲገዛ ከመመኘት ያለፈ የምናበረክተው አስተዋፅኦ አለ፡፡
በትውልዳችን እንዴት መኖር እንዳለብን ካወቅን በኋላ የምናስበው ስለሚመጣው ትውልድ ነው፡፡ እኛ ደስ ብሎን የተገዛንለት ጌታ ዘራችንም እንዲገዛለት ጥማታችን ነው፡፡ ለሚመጣው ትውልድ ለጌታ እንዲገዛ ከመመኘት ያለፈ የምናበረክተው አስተዋፅኦ አለ፡፡
ዛሬ በምንኖረው ኑሮ ለትውልዳችን ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚሆነ ነገር መስራት መልካመ አሻራ መተው ይጠበቅብናል፡፡ ከራሳችንና ከዘመናችን ያለፈ ለሚመጣው ትውልድ ሃላፊነት አለብን፡፡
ነገር የወደፊቱ ትውልድ በተሻለ እግዚአብሄርን እንዲያመልክ ፣ በተሻለ ሁኔታ ጌታን እንዲከተልና እግዚአብሄርን በሙላት እንዲያገለግል በዘመናችን በምንናገረው ንግግር ብቻ ሳይሆን በምንኖረው ኑሮ ልናመቻችለት እንችላለን፡፡ የሚመጣው ትውልድ በተግባር እግዚአብሄር እንዴት እንደሚመለክ በንግግር ብቻ ሳይሆን እያየ ተግባራዊ ትምህርት ሊማር ይችላል፡፡
አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡10
ለሚመጣው ትውልድ ጌታን በሚገባ የመከተል ሞዴል ልንሆንለት እንችላለን፡፡ በእያንዳንዱ ቀን በምንኖረው ኑሮ የሚመጣው ትውልድ ለእግዚአብሄር ቃል የመጀመሪያውን ስፍራ እንዲሰጥ ምሳሌ ልንሆነው እንችላለን፡፡ ከእያንዳንዱ ኑሯችን እግዚአብሄርን ስለማመን ተግባራዊ ልምድ በመቅሰም ስኬታማ የሚያደርገውን መልካም ምሳሌ ልንተውለት እንችላለን፡፡
አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። ዘዳግም 6፡1-2፣6-7
በዚህ ሁኔታ ነው እግዚአብሄርን የሚያመልክ በእምነት የሚኖር ተከታታይ ትውልድ ማፍራት የምንችለው፡፡
በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡5
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
No comments:
Post a Comment