Popular Posts

Friday, September 30, 2016

የሰው ፍቅር

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1 ቆሮንቶስ 131

ሰው የሚያከብረውም ሆነ የሚያዋርደው ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ያለው ሰው የከበረ ሰው ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ደግሞ የተዋረደ ነው፡፡

ሰው የተሰራው ለፍቅር ነው፡፡ ሰው የተሰራበት አላማ ከጎደለው ባዶ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በመጀመሪያ እግዚአብሄርን እንዲወድ እንዲሁም ሰውን እንዲወድ ነው ፡፡

አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ማርቆስ 12፡30-31

ሰውን የሚያከብረው የፍቅር ድርጊት ነው፡፡ ሰው ምንም ችሎታ ቢኖረው በፍቅር ልብ ካላደረገው ምንም አይጠቅመውም፡፡ ሰው ለእግዚአብሄርም ሆነ ለሰው ምንም ስጦታ ቢሰጥ ከፍቅር ልብ የመነጨ ስጦታ ካልሆነ ከንቱ ነው፡፡

በፍቅር ያልሆነ የሰው ተሰጥኦ ከንቱ ነው፡፡ ሰው ታላቅ የመናገር ስጦታ ቢኖረው እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽልና እንደሚጮኽ ናስ ትርጉም የሌለው ረባሽ ነው፡፡  

ሰው ፍቅር ከሌለው ለማንም አይጠቅምም፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ለራሱም ምንም አይጠቅመውም፡፡

ሰውን የሚያከብረው ፍቅር ስለሆነ ሰው በአለም ላይ አለ የሚባለው እውቀት ቢኖረው ፍቅር ግን ከሌለው ከንቱ ነው፡፡
የሰውን መስዋዕትነት የሚያከብረው ከፍቅር ልብ መምጣቱ ነው፡፡ ሰው ድሆችን ለመመገብ ታላቅ መስዋዕትነት ቢከፍል ከፍቅር ልብ የመነጨ ግን ካልሆነ ዋጋ የለውም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes


#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment