Popular Posts

Saturday, May 20, 2023

ፍጹማን ሁኑ

 

ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 5:43-48

ኢየሱስ እንዲህ አለ " እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ "

እነዚህን ቃል የተናገረው እኛን የሚያውቀን ኢየሲስ ነው፡፡ ፍፁማን ሁኑ ብሎ ያዘዘን ምን እንደሰጠን በሚገባ የሚያውቀው ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ ይህን ያዘዘው አፈጣጠራችንን ድካማችንን ብርታታችንን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው፡፡  

እግዚአብሔር ሲናገር ከልቡ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለቀልድ አይናገርም፡፡

እግዚአብሔር ካዘዘ ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር የማይቻል ነገር አያዝም፡፡

ስለእኛ ሊመሰክር የማይችለውን የሚሰማንን ስሜት ትተን እንደታዘዝነው ፍፁማን እንሁን፡፡

ዙሪያችን የሚሰማውን የአካባቢያችንን ድምፅ ትተን ፍፁማን ሁኑ የሚለውን የጌታን ቃል እንታዘዝ፡፡

ሰው ብዙ ነገር ብሎ ሊሳሳት ይችላል፡፡ ሰው ግን እግዚአብሄር ያለውን ብሎ አይሳትም፡፡ እንደተሳሳትን ቢሰማንም እንኳን እግዚአብሔር የሚለውን በድፍረት እንበል፡፡

ፍፁም መሆን እችላለው ማለት ትእቢት ሳይሆን ትህትና ነው፡፡ እንዲያውም ትእቢት የሚሆነው ፍፁም መሆን አልችልም ማለት  ነው፡፡ ፍፁም መሆን አልችልም ማለት እግዚአብሄር ያዘዘው ነገር መፈፀም የማይቻል ነገር ነው ብሎ እግዚአብሔርን እንደማማት ይቆጠራል፡፡

ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡ 30-31

ባይገባንም ባንረዳውም እንኳን እግዚአብሔር ያለውን አሜን እሆናለሁ ብሎ እንደመቀበል ያለ ነገር የለም፡፡

የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።

አሜን ፍፁም እሆናለሁ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 


No comments:

Post a Comment