Popular Posts

Friday, May 12, 2023

ከምናስበው በላይ ብዙ ጥቃቶች መንፈሳዊ ናቸው

 


በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1 የጴጥሮስ መልእክት 58-9

የመንፈሳዊው አለም ውጊያ እውን ነው፡፡ በመንፈሳዊው አለም ውጊያ አለ፡፡ የህይወት ጠላት የሆንው ሰይጣን ዲያቢሎስ ይዋጋል፡፡

ብዙ ጊዜ ግን ነገሮች ሲበላሹ አስቀድመን የምናስበው የመንፈሳዊውን ውጊያ አይደለም፡፡ ቀድመን በሳይንስ ወይም በባህል ልንተረጉመው እና ልንፈታው እንፈልጋለን፡፡ ወይም ደግሞ በባህሪ ወይም በስነልቦና ልንተረጉመው እንፈተናለን፡፡

መንፈሳዊ ውጊያ ሊሆን እንደሚችል የምናስበው በተያየ መንገድ ልንተረጉመው ሞክረን መፍታት ሲያቅተን ብቻ ነው ፡፡

ነገር ግን በህይወታችን ያሉ ብዙ ጥቃቶች ከምናስበው በላይ መንፈሳዊ ጥቃቶች ናቸው፡፡ ሰይጣን በህይወታችን አቅጣጫ ሁሉ ከምናስበው በላይ ይዋጋናል፡፡ አንዳንዴ በዚህ አይመጣም ብለን በምናስብብት መንገድ ሁሉ ሊያጠቃን ይመጣል፡፡

ኢየሱስን ከፈተነው በኋላ ዲያቢሎስ ለጊዜው ብቻ እንደተለየው ሰይጣን ለጊዜው ቢለየን እንኳን በሌላው የህይወታችን ዘርፍ ተመልሶ እንደሚመጣብን ማወቅ ንቁ እንድንሆን ያስችለናል፡፡ በነቃን ቁጥር እና ሃሳቡን ባልሳተው መጠን በትጋት ስለምንቃወመው አሸናፊዎች እንሆናለን፡፡

በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፥11

ዲያቢሎስ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ምን ያህል ሊያጠቃን በትጋት እንደሚዞረን ከተረዳን ለዲያቢሎስ ፈንታ አንሰጠውም፡፡

ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡27

በቀጣይነት በውጊያ ላይ እንዳለን አውቀን መንቃት ይገባናል፡፡

በህይወታችን የሚያነጣጥረውን የዲያቢሎስን ጥቃት ጸንተን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መቋቋም ይጠይቃል፡፡

እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡7

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 


No comments:

Post a Comment