ፀሎት ከእግዚአብሄር የተሰጠ ታላቅ እምቅ ጉልበት
ያለው ውጤታማ መንፈሳዊ ስራ ነው፡፡
የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
የያዕቆብ መልእክት 5፡16
ውጤታማ ፀሎትን ለመፀለይ መረዳት ያለብንን ነገሮችን
ከእግዚአብሄር ቃል እንመለከታለን፡፡
በመጨነቅ ምንም ውጤት ስለማናመጣ ከመጨነቅ ይልቅ
ብንፀልይ ለጭንቀት የምናወጣውን ጉልበት ለፀሎት ብንጠቀምበት ህይወታችን ፈፅሞ ይለወጣል፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6
በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት የምናምን ሁላችን
የልጅነት ስልጣን ተሰጥቶናል፡፡
ፀሎት ከአባት ጋር የሚደረግ የልጅ ንግግር ነው፡፡
ፀሎት የልጅነት መብት ነው፡፡ እግዚአብሄር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ በኩል ልጆቹ አድርጎናል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
እግዚአብሄር ተቀብሎናል፡፡ እግዚአብሀር ዙፋን
ፊት ቀርበት ጉዳያችንን የማስፈፀም መብት ተሰጥቶናል፡፡
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16
በክርስቶስ የመስቀል መስዋእትነት በኩል እግዚአብሄር
በክርስቶስ ባለነው በእኛ ደስተኛ ነው፡፡
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት
ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17
ካለበታችነት ስሜት ካለፍርሃት እና ካለመሸማቀቅ
በእግዚአብሄር ፊት ለመቅረብ የእግዚአብሄር ፅድቅ ሆነናል፡፡
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን
ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡21
ውጤታማ ፀሎት የሚጀምረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ
ከማወቅ ነው፡፡
በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
የፀሎት ትልቁ ክፍል ስላለንበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን
ፈቃድ መፈለግ እና ማወቅ ነው፡፡ ውጤታማ ፀሎት የሚጀምረው ስላለንበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከእግዚአብሄር ቃል ፈልጎ ከማግኘት
ነው፡፡ በፀሎት ለእግዚአብሄር መናገር የሰከንዶች ስራ ነው፡፡ ትልቁን
ጊዜያችንን የሚወስደው ስለምንፀልየው ነገር ከእግዚአብሄር ቃል መረዳትን ማግኘት ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17
በእርሱ
ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን
ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
ፀሎት
የሚጀምረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ያገኘን ጊዜ ነው፡፡ የእግዚአብሄን ቃል እያጠናን መረዳቱ ሲመጣልን ልንፀልይ እና ሊመለስልን ይችላል፡፡
ስንፀልይ
በምስጋና መፀለይ አለብን
ስንፀልይ
እግዚአብሄር አባታችን እንደሆነ መልካም እንደሚያደርግልን ከዚህ በፊት መልካም ሲያደርግልን እንደቆየ በምስጋና ልብ መፀለይ አለብን፡፡
እግዚአብሔር
እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።
ወደ
ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙረ ዳዊት 100፡4
ስንፀልይ
በእረፍት መፀለይ አለብን
አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። የማቴዎስ ወንጌል 6፡7-8
ስንፀልይ
የፀሎት ርእሱን ለመናገር መቸኮል የለብንም፡፡ ስንፀልይ ለጌታ ካልነገርነው አያውቅም በሚል አስተሳሰብ መፀለይ የለብንም፡፡
ስንፀልይ
በእግዚአብሄር መንፈስ በመደገፍ መፀለይ ውጤታማ ያደርገናል፡፡ በአእምሮዋችን ያለውን ፀሎት ሳይሆን ጌታ አሁን እንድንፀልይ የሚፈልገውን
መፀለይ ውጤታማ ያደርገናል፡፡ አሁን በእውነት የሚያስፈክገንን ለመፀለይ በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ በፀሎት ቦታችን ልባችንን መስማት
አለብን፡፡ መንፈስ ሲመራን በአእምሮዋችን የሌለውን ነገር ወደ ልባችን ያመጣዋል፡፡ አንዳንዴ ለራሳችን ልንፀልይ ብለን ለሌሎች እንድንፀልይ
ይመራናል፡፡
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡26-27
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment