Popular Posts

Saturday, May 20, 2023

እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር

 


ኤልሳዕም። ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ አለው፤ ቀስቱንና ፍላጻዎችንም ወሰደ። የእስራኤልንም ንጉሥ። እጅህን በቀስቱ ላይ ጫን አለው። እጁንም ጫነበት፤ ኤልሳዕም እጁን በንጉሡ እጅ ላይ ጭኖ። የምስራቁን መስኮት ክፈት አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም። ወርውር አለ፤ ወረወረውም። እርሱም። የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው፤ በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያዊያንን በአፌቅ ትመታለህ አለ። ደግሞም። ፍላጻዎቹን ውሰድ አለው፤ ወሰዳቸውም። የእስራኤልንም ንጉሥ። ምድሩን ምታው አለው። ሦስት ጊዜም መትቶ ቆመ። የእግዚአብሔርም ሰው ተቆጥቶ። አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ኖሮ ሶርያን እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ አለ። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 13:18-18

ይህ የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል የሚያስተምረን የእስራኤል ንጉስ በነቢዩ አማካኝነት ስለደረሰው የውጊያ ስልት መልእክት ነው፡፡ ንጉሱ በነቢዩ ተመርቶ በምሳሌነት ሶስት ጊዜ ብቻ ፍላፃውን እንደወረወረ እና እንዳቆመ ከዚህ ክፍል እንመለከተታለን፡፡ እግዚአብሄር ግን በነቢዩ በኩል ሲናገረው ሶስት ጊዜ ብቻ ባትመታ ኖሮ ጠላቱን ፈፅሞ ያጠፋ እንደነበር መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

ይህ ክፍል የሚያስተምረን ጠላትን ፈፅመን እንድንመታ ነው፡፡ ብንሰንፍ እና ጠላትን ፈፅመን ለመምታት ቸል ብንል ጠላታችንን ፈፅመን በመምታት ሙሉ ድልን እንዳናገኝ የማግኘት እድላችንን በከንቱ እናባክነዋለን፡፡

እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 10፡19

በተለይ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የዲያቢሎስን ስልጣን ገፎታል፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችል ላደረግነው በጠላት ላይ ስልጣን ተሰጥቶናል፡፡

አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15

ጠላትን መቃወም እና የጠላትን ምርኮ ፈፅመን መበዝበዝ አለብን፡፡ ነገር ግን ጠላትን ተዋግተን ለማሸነፍ ቸል ብንል እንደሚገባን ማሸነፍ እንደማንችል እና የድሉን አክሊን መጎናፀፍ እንደማንችል መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። የማርቆስ ወንጌል 3፡27

እና ጦርነትን እንዳካሄደ እና ነገር ግን የሚገባውን ያህል በጠላቱ ላይ ስላልጨከነ የሚገባውን ያህል ድል እንዳላገኘ ከዚህ ክፍል እንማራለን፡፡

በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 610-12

በህይወታችን ዲያቢሎስን መቃወም አለ፡፡ ዲያቢሎስን ፀንቶ መቃወም ደግሞ አለ፡፡ ሙሉ ድል የሚያስገኘው ዲያቢሎስን ፀንቶ መቃወም ብቻ ነው ፡፡

በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡9

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 


No comments:

Post a Comment