Popular Posts

Wednesday, May 3, 2023

ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ ጨምሩ

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።2 ጴጥሮስ 13-11

የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ፍሬያመ ለመሆን መቀጣጠልን እና ከፍተኛ ፍላጎትን ይጠይቃል፡፡ ካለታላቅ ፍላጎት እና ቅናት በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አይቻልም፡፡ ከላይ ባለው ጥቅስ እንደምንመለከተው ሃዋርያው ጴጥሮስ በመንግሥቱ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልገንን ጥረት እና ትጋት ለማጉላት የሚከተሉትን ቃላት ሲጠቀም እናያለን፡፡

ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ  . . . ምሩይለናል፡፡ ቁጥር 5

ትዕዛዙን እንደገና አጽንዖት ተሰጥቶታል፡፡

ከፊት ይልቅ ትጉቁጥር #10

ሃዋርያው እነዚህን እግዚአብሄራዊ ባህሪያት በህይወታችን እንዲኖረን እና እንዲበዙልን ብርቱ ፍላጎት እና ቅናት ማሳየት እንዳለብን ያሳስበናል፡፡ ሃዋሪያው እነዚህ ባህሪያት ለእኃ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን የእነዚህ ባህሪያት ሲበዙልን ምን ምን ጥቅሞች እንዳሉት በመዘርዘር ያሳስባል፡፡

“እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ” ቁጥር 8

ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልቁጥር 8

ከከንቱነት መጠበቅ እንዴት ድንቅ ነገር ነው? በሁሉም የህይወታችን ዘርፎች ፍሬያማ እና ምርታ መሆን እንፈልጋለን። እግዚአብሄር በሰጠን እምቅ ሃይል ሁሉ ስኬታማ መሆን እንፈልጋለን። በምድር ላይ የሚኖረንን አንድ እድል በከንቱ ማባከን አንፈልግም። ጉልህ የሆነ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖረን እንፈልጋለን። ታዲያ ብርቱ ፍላጎታችን እና ትጋታችን ብቻ ውጤታማ እንድንሆን ያደርገናል።

ቅዱሳት መጻህፍትመጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድቁጥር 8 በማለት በግልጽ እንደሚያስተምሩን በጋለ ስሜት እና በትጋት መጠራታችን እና መመረጣችንን ማፅናት እንችላለን፡፡

እነዚህ የክርስቲያን ባህሪያት ለእኛ ሆነው ቢበዙ ጥሪያችንን ማረጋገጡ እና ማፅናቱ ብቻ አይደለም መፅሃፍ “እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም” ቁጥር 8 እንደሚል እንዳንሰናከልም ዋስትና ይሰጣል።

 በመቀጠልም “ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል” በማለት ትጋት አማራጭ የሌለው ነገር እንደሆነ በብርቱ ይመክራል።

ለደህንነታችን ትክክለኛ አመለካከት ያለመያዝ እና መለኮታዊ ባህሪ ተካፋይ የመሆናችንን እውነታ በትክክል ያለመረዳት አደጋ ትልቅ ነው። ይህ አመለካከት ከቅርብ እይታ ወይም ከዓይነ ስውርነት የመነጨ አደጋ ነው።

እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል” ቁጥር 9

የሚገባውን ያህል ቅናት የሌለው ሰው ምልክት የተደረገለትን ታላቅ ይቅርታ በትክክል አለመገንዘብ እና አለማድነቅ ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ማዳን እንደ ቀላል ነገር ካየው ለእግዚአብሄር ነገር በሚገባ ለመትጋት ቅናት እና ግለት አይኖረውም በህይወቱ የሆነው የሃይማኖት ለውጥ ብቻ እንጂ የመንግሥት ለውጥ እንደሆነ አያስብም። እግዙአብሄር ግን ከታላቅ ሞት አድኖናል፡፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን ወደ ፍቅሩም ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1:13

ቅናት የሌለው ክርስትያን ችግር በህይወቱ የሆነው የጌቶች ለውጥ መሆኑን በሚገባ አለመረዳቱ ነው

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ኤፌሶን 21-3

የእግዚአብሔር መንግሥት ልበ ደካሞች እና የልፍስፍሶች አይደለችም።

ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ማቴዎስ 1112

ኢየሱስ ለብ ያልክ ነህ እንጂ በራድ ወይም ትኩስ አይደለህም ብሎ የሚወቅሰው ስለዚህ ነው፡፡ በራድ ወይም ትኩስ ስላልሆንክ ልተፋህ ነው ይላል እግዚአብሄር በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ለብ ያለ ወይም ገለልተኛ መሆን በፍፁም የተለመደ ነገር አይደለም። ሳይሰስት በልግስና የመለኮታዊ ባህሪ ተካፋዮች ባደረገን በእግዚአብሄር አይን ለብ ያለ መሆን ቀዝቃዛ ከመሆን ምንም አይሻልም፡፡ ቅናት እና ብርቱ ጥማት ማጣት  ወደ ኋላ የመመለስ ያህል አደገኛ ነው። እግዚአብሄር የሚቀበልው አንድ እና ብቸኛ ነገር ቅናት እና ትጋትን ብቻ ነው።

እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። ራእይ 316

ተገቢውን ትጋት ያለማሳየት ድክመቶች የሚመነጩት የሃጢያትን ይቅርታ ካለመረዳት ነው፡፡  

ሃዋርያው ጴጥሮስ የእግዚአብሄርን ነገር በትጋት የማይጨምር ሰው የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአልቁጥር 9 ይላል፡፡

ለእግዚአብሔር ነገር ከፍተኛ ፍቅር እና ግለት የማያሳይ ሰው የቀደመውን ኃጢአቱን መንጻት መርሳቱ ግልፅ ነው፡፡

ትጋትን ሁሉ ማሳየት የእግዚአብሔር መንግሥት ትክክለኛ መርህ ነው። የእግዚአብሔርን መንግሥት መስፈርት ጠብቀን እንኑር።

አብይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa 

 

No comments:

Post a Comment