Popular Posts

Friday, May 26, 2023

የፀሎት ያለህ !

 


ስለአንድ ነገር ውጤታማ ለመሆን የእግዚአብሄርን ልብ ማግኘት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም ይለናል፡፡ ነገር ግን በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እንደተረከው መፅሃፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሄርን ልብ ሊተርክ የሚችል ኢየሱስ ነው፡፡

መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።የዮሐንስ ወንጌል 1፡18

ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ባለጠግነት ያውቃል፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሄር ለህዝቡ ያለውን የአባትነት የፍቅር ልብ ያውቃል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ህዝብ ምን ያህል በፀሎት ሊጠቀም እንደሚችል ያውቃል፡፡

ሰው ግን የእግዚአብሄርን ልብ ካልተረዳ በእጦት ውስጥ ሊኖር እንደሚችል ደግሞ የሰውን ሁኔታ ያውቃል፡፡ ሰው በፀሎት ጠይቆ መቀበል ሲችል በእጦት ሊሰቃይ እንደሚችል የሚያውቀው ኢየሱስ በብዙ ቦታ ስለፀሎት በተደጋጋሚ ተናግሮዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ልብ የሚያውቀው ኢየሱስ ሰው በፀሎት የእግዚአብሄርን ባለጠግነት መካፈል እንደሚችል  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲያበረታታ እንመለከታለን፡፡

ከእነዚህ ጥቂት ጥቅሶች እግዚአብሔር ስለፀሎት ያለውን የእግዚአብሄርን ልብ እንመለከታለን፡፡

እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16፡24

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የዮሐንስ ወንጌል 1623፡7-8

በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። የዮሐንስ ወንጌል 16፡24

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። የማርቆስ ወንጌል 11፡24

ከኢየሱስ ትምህርት እና ህይወት እግዚአብሄር የሰውን ፀሎት ለመመለስ ያለውን የቅናት ልብ በቀላሉ እንመለከታለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 

 


No comments:

Post a Comment