Popular Posts

Tuesday, October 1, 2019

ሥራውም ሁሉ በእምነት ነው


               
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙረ ዳዊት 334         
እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በቁሳዊው አለም አይገኝም፡፡ እግዚአብሄርን በቁሳዊው አለም ልናገኘው ልናናግረው ልንዳስሰው ልንደርሰው የሚያስፈልገንን ነገር ከእርሱ ልንቀበል አንችልም፡፡ እግዚአብሄርን እግዚአብሄር ለህይወታችን ያለውን ነገር ማየት የእግዚአብሄርን ነገር መድረስ እና ከእግዚአብሄር መቀበል የምንችለው በእምነት ነው፡፡ 
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በእምነት ከእርሱ ጋር እንዲገናኝ አድርጎ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚሰራው በእምነት ነው፡፡
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ወደ ዕብራውያን 11፡1
ካለ እምነት እጅ እግዚአብሄርን መድረስ አንችልም፡፡ ካለ እምነት አይን የእግዚአብሄርን ነገር ማየት አንችልም፡፡ ካለ እምነት እጅ ከእግዚአብሄር መቀበል እንችልም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው። የማቴዎስ ወንጌል 21፡21-22
ካለእምነት እግዚአብሄርን ልናገኘው አንችልም፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር ጋር አብረንም መጓዝ አንችልም፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አንችልም፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6
ካለ እምነት የሆነ ነገር ሁሉ ሃጥያት ነው፡፡
በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23
ምንም የሃይማኖት ወጎችን ብንፈፅምም ካለእምነት ግን ከእግዚአብሄር ጋር እግዚአብሄርን መገናኘት እና እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ነገር መቀበል አንችልም፡፡
እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት። የማርቆስ ወንጌል 5፡34
ኢየሱስ እንኳን በምድር አገልግሎቱ በእምነት ያልተቀበሉትን ሰዎች መፈቀስ አልቻለም፡፡
በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም። የማቴዎስ ወንጌል 13፡58
በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም። ስለ አለማመናቸውም ተደነቀ። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር። የማርቆስ ወንጌል 6፡5-6
እግዚአብሄርን ተጠራጥረን ከእግዚአብሄር የምናገኘው ነገር የለም፡፡
ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። የያዕቆብ መልእክት 1፡6-8
የእግዚአብሄር መንገድ ሁሉ በእምነት እና በቅንነት ቃሉን በማመን እንጂ በብልጠትና በጥርጥር አይደለም፡፡  
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙረ ዳዊት 33፡4    
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

No comments:

Post a Comment