Popular Posts

Friday, October 18, 2019

ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል



ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። መዝሙረ ዳዊት 23፡6
እግዚአብሄር ፈጣሪያችን ነው፡፡ እኛ ለእግዚአብሄር ተፈጥረናል፡፡ እኛ የእግዚአብሄር ነን፡፡ እግዚአብሄር የህይወታችን ባለቤት ነው፡፡
እኛ የእግዚአብሄርን ቸርነትና ምህረት ለማግኘት ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር የእኛን ምህረትና ቸርነት ማግኘት ይፈልገዋል፡፡
በእኛ ቸርነቱንና ምህረቱን በመከተል ላይ ብቻ እግዚአብሄር አይተማመንም፡፡ እኛ የመከተል ችሎታችን እንከን የለሽ ስላይደለ የእግዚአብሄርን ምህረትና ቸርነት ብንከተል በትክክል ላንከተለው እንችላለን፡፡ እኛ እውቀታችን ፍፁም ስላይደለ የእግዚአብሄርን ምህረትና ቸርነት በትክክል ላንከተል ልንሳሳት እንችላለን፡፡
እግዚአብሄር የምህረትና የቸርነትን ነገር ለእድል አልተወውም፡፡ እግዚአብሄር የቸርነትና የምህረትን ነገር ለእኛ ፍፁም ያልሆነ ችሎታም አልተወውም፡፡ ምህረትና ቸርነት እኛን የመከተሉን ነገር እግዚአብሄር ራሱ የሚያደርገው ሃላፊነቱ አድርጎ ወስዶታል፡፡
እግዚአብሄር ግን እንደ ህይወታችን ባለቤት በምህረትና በቸርነት ከተከተለን ምህረትና ቸርነት ያገኙናል እንጂ አይስቱንም፡፡
አንድ ሰው በህልሙ አባቱ እጁን ይዞት አየ፡፡ ህልሙ ሲፈታለት እኔ አግዚአብሄር አባተህ እጅህን ይዤሃለሁ፡፡ አንተ እጄን ብትይዘኝ በመንገድ ላይ ከፍታና ዝቅታ ልትለቀኝ ትችላለህ፡፡ አንተ ምንም አስቸጋሪ ነገር ውስጠ ብታለፍ እኔ ስለያዝኩህ አስተማማኝ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚይዘን እስከጊዜው አይደለም፡፡ ከማኅፀን እስካሁን የተሸከመን እግዚአብሄር እስከሽምግልና ይሸከመናል፡፡
እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፥ ስሙኝ። እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 46፡3-4
በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡6
እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል። ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 17-9
ህይወታችንን ዘመናችንን የሰጠነው እግዚአብሄር ታማኝ ነው፡፡
ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፥ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፥ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡12
ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። መዝሙረ ዳዊት 236
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ቸርነት #ምሕረት #ሽምግልና #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #አስተምርሃለሁ #መንገድ #እመራሃለሁ #ዓይኖቼን #አጠናለሁ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment