Popular Posts

Monday, October 14, 2019

ይታክቱማል



ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡30
ሰው ይቸኩላል፡፡ ሰው አይጠብቅም፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ ነገሮች ወዲያው እንዲሆኑለት ይፈልጋል፡፡
ሰው አዲስ ነገር ሲያገኝ ይፈነጥዛል ነገር ግን ወዲያውም ይሰለቻል፡፡ በሰው ዘንድ ክብሩን ጠብቆ የሚቆይ ነገር የለም፡፡ ሰው የተመኘውን ነገር ሲያገኘው ክብሩን ያጣዋል፡፡ በሰው ዘንድ የከበረ ነገር በእጅ ሲያዝ ዋጋው ይቀንሳል ይረክሳል፡፡
ሰው ለጥቂት ሊፀና ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰው ለረጅም ጊዜ የመፅናት ችሎታ የለውም፡፡
ሰው ወዲያው ይሰለቻል፡፡ ሰው ሃይሉ ያልቃል ይደክመዋል፡፡ ማንም ሰው ወጣቱ ትኩስ ጉልበት ያለውም ቢሆን ይታክታል፡፡
እግዚአብሄር ብቻ ለደካማ ሃይልን ይሰጣል፡፡ ብርታት ለሌለው ጉልበትን ይጨምራል፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡29
እግዚአብሄር ለደካማ ሃይልን በመስጠት ሰው እንዲጠብቅ ያስችለዋል፡፡ ሰው እንዳይቸኩል እና ሰልችቶት ጥሎ እንዳይሄድ ልቡን የሚይዘው የእግዚአብሄር ፀጋ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚያስችለውን የእግዚአብሄርን ሃይል የሚቀዳው እግዚአብሄርን ከመጠበቅ በእግዚአብሄር ፊት በፀሎት ከመቆየት ብቻ ነው፡፡   
እግዚአብሄር ግን እንዲህ ይላል፡፡ ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡30-31
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #መጠበት #መተማመን #እምነት #ያድሳሉ #ይወጣሉ #አይደክሙም #አይታክቱም #እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment