Popular Posts

Thursday, October 3, 2019

ሁለቱ አይነት መንፈሶች



በአለም ላይ ብዙ መንፈሶች አሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ አይነት መንፈሶች የሉም፡፡ በአለም ላይ ያሉት መንፈሶች ሁለት አይነት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን አይነታቸው ሁለት አይነት ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሄር መንፈስ አለ፡፡ የሰይጣን መንፈስ አለ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ መንፈስ ነው፡፡ የሰይጣን መንፈስ ደግሞ እርኩስ መንፈስ ነው፡፡
መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥ 1 ወደ ጢሞቴዎስ 4፡1-2
ከእግዚአብሄርና ከሰይጣን መንፈሶች መካከል ገለልተኛ መንፈስ የለም፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ ያልሆነ የሰይጣንም መንፈስ ያልሆነ ገለልተኛ መንፈስ የለም፡፡
የእግዚአብሄር መንፈስ ካልሆነ የሰይጣን መንፈስ ነው፡፡ የሰይጣን መንፈስ ካልሆነ የእግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ ቅዱስ መንፈስ ካልሆነ እርኩስ መንፈስ ነው፡፡ እርኩስ መንፈስ ካልሆነ ቅዱስ መንፈስ ነው፡፡
ገለልተኛ መንፈስ እንደሆነ ሊያሳምን የሚፈልግ መንፈስ አለ፡፡ የሰይጣን መንፈስ በግልፅ አይሰራም፡፡ የሰይጣን መንፈስ ገለግለተኛ መንፈስ መስሎ በድብቅ ይሰራል፡፡ የሰይጣን መንፈስ በሃይማኖት በባህል ጀርባ ተሸሸጎ እንጂ በግልፅ አይሰራም፡፡
በግልፅ አይሰራም
የሰይጣንን እና የእግዚአብሄርን መንፈስ እንዴት መለየት እንችላን፡፡
1.      የእግዚአብሄር መንፈስ ከእግዚአብሄር ቃል ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ትምህርትና ተግባር በእግዚአብሄር ቃል ተፈትኖ ያልፋል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል በተለይ በአዲስ ኪዳን አስተምሮት ሊደገፍ የማይችል ማንኛውም አስተሳሳብና ልምምድ ከእግዚአብሄር መንፈስ አይደለም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ጋር የማይስማማ ትምህርት ሁሉ ከሰይጣን ነው፡፡
መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡1-2
2.     የእግዚአብሄር መንፈስ የሚደረስበት በኢየሱስ ብቻ ነው
የእግዚአብሄር መንፈስ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ በየትኛውም ሃይማኖት በኩል አይገኝም፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ የሚገኘው በኢየሱስ የመስቀል ስራ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ የሚገኘው ኢየሱስ  ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በመሞት ዋጋን እንደከፈለ በማመን ብቻ ነው፡፡
ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡6
3.     የሰይጣን መንፈስ ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ እንጂ ስለሌላ አይመጣም
የሰይጣን መንፈስ ሃብት ዝና ስልጣን እሰጣችኋለሁ በማለት ሰዎችን በማታለል ሰዎች ያላቸውንም መንፋሰዊ ሃብት ሰላም ደስታ እርካታ ይሰርቃል፡፡ ሰይጣን ከሰላምና ከገንዘብ ሰላም እንደሚበልጥ ያውቃል፡፡ ሰይጣን ከእረፍትና ከስልጣን እረፍት እንደሚበልጥ ያውቃል፡፡ ሰይጣን ከእርካታና ከዝና እርካታ እንደሚበልጥ ያውቃል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ሃብት ዝና ስልጣን እሰጣችሁዋለሁ በማለት የሚበልጠቅውን ሰላም ደስታና እርካታቸውን ይሰርቃል፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
የእግዚአብሄር መንፈስ ህይወትን ሊሰጥ ሊባርክ ሊያበዛ ሊጠቅም ይመጣል፡፡
እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
4.     የእግዚአብሄር መንፈስ ኢየሱስን ያከብራል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ሰውን ዝነኛ ለማድረግ አይመጣም፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ከሆነ የሚያከብረው ኢየሱስን ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ የሰዎችን ትኩረት ከእግዚአብሄር እና ከኢየሱስ አይመልስም፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ የሰዎችን ትኩረት ወደ ኢየሱስ ይመልሳል፡፡
ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። የዮሐንስ ወንጌል 16፡13-14
5.     የእግዚአብሄር መንፈስ በፍቅር ይሰራል
በሰዎች መካከል ጠብን የሚዘራ ጥላቻን የሚያስፋፋ የእግዚአብሄርን መንፈስ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ፍቅርን ይቅር ባይነትን ምህረትን በጎነትን ያስፋፋል፡፡
እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡16
6.     የእግዚአብሄር መንፈስ የሰይጣንን መንፈስ ይገዛል
የሰይጣን መንፈስ ለኢየሰስ ስም ይገዛል፡፡ ሰዎችን የያዘ የሰይጣን መንፈስ በኢየሱስ ስም ይለቃል፡፡ ሰይጣን የተፈረደበት ስለሆነ ፍርዱን እየጠበቀ ያለ ፍርደኛ ነው፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሔርመንፈስ #እርኩስመንፈስ #ሰይጣን #ፈትኑ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነቢያት #ነቢይ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment