የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። የያዕቆብ መልእክት 1፡20
የእግዚአብሄርን ፅድቅ ለመስራት የሚፈልግ የሰው ቁጣ አይሳካለትም፡፡ የሰው ቁጣ
የእግዚአብሄ ፅድቅ ለመስራት አቅም ያነሰዋል፡፡ የሰው ቁጣ ለእግዚአብሄር ፅድቅ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ ነው፡፡
የሰው ቁጣ የእግዚአብሄር እጅ የሌለበት ሰው በራሱ በስጋው ሃሳብ ተነሳስቶ የሚቆጣው
ቁጣ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ቁጣ እግዚአብሄር ራሱ ሲቆጣ የሚቆጣው ቁጣ ነው፡፡ እውነት ነው የእግዚአብሄር
ቁጣ በሰው አማካኝነት ይገለጣል፡፡ የእግዚአብሄርን ቁጣ በትክክል ተረድተው ከእግዚአብሄር ጋር አብረው የሚቆጡ ሰዎች የሚቆጡት ቁጣ
የእግዚአብሄር ቁጣ እንጂ የሰው ቁጣ አይደለም፡፡
እውነት ነው የእግዚአብሄር ቁጣ በሰው ውስጥ የሚገለጥበት ጊዜ አለ፡፡ ነገር ግን
ሰው በተቆጣ ቁጥር እግዚአብሄር ተቆጣ ማለት ግን አይቻለም፡፡ ሰው ከራሱ ግላዊ ፍላጎት ተነስቶ ሊቆጣ ይችላል፡፡ ሰው ከራሱ የእውቀት
እና የማስተዋል ማነስ የተነሳ ሊቆጣ ይችላል፡፡
አንዳንደ ጊዜ በአንዳነድ ሰው ላይ ልባችን ያዝናል፡፡ በግል እኛን ያደረገን ምንም
ነገር የለም፡፡ ወይም በዚያ ሰው ላይ እንደናዝንበት የተለየ በደል አላደረሰብንም፡፡ ነግር ግን ልባችን ካለ ምክኒያት ያዝናል ይቆጣል፡፡
እግዚአብሄር በልባችን ቁጣውን ካካፈለን ከእግዚአብሄር ጋር ተባብረን አብረን መቆጣት ይገባናል፡፡ የእግዚአብሄር ቁጣ ነገሮችን ያስተካክላል፡፡
በራሳችን ተነሳሰተን የምንቆጣው ቁጣ ግን ነገሮችን ለማስተካከል አቅም የለውም፡፡
የሰው ቁጣ የእግዚአብሄርን ቁጣ የማይሰራበትን ምክንያት እንመልከት
1.
የሰው ቁጣ የሚመሰረተው በሰው ውስን እውቀት ላይ ነው፡፡ እግዚአብሄር
እግዚአብሄ ለሰው የሰጠውን ስለሚያውቅ እና እንደተሰጠው መጠን እንዳልኖረ በትክክል ስለሚመዝን እግዚአብሄር ሲቆጣ በትክክል ይቆጣል፡፡
የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ
እጅግ ይገረፋል፤ ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥
ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል። የሉቃስ ወንጌል 12፡47-48
2.
የሰውን ድካምና ጥንካሬ ስለሚያውቅ የእግዚአብሄር ቁጣ በትክክል ሊፈርድ
ይችላል፡፡
ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው
እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው
ሄደ። የማቴዎስ ወንጌል 25፡14-15
3.
ሰውን ሁሉ እኩል ስለሚያይና ለማንም ስለማያዳላ የእግዚአብሄር ቁጣ
ትክክለኛ ቁጣ ነው፡፡ የሰው ቁጣ ከሌላው ሰው አላግባብ ጥቅምን ፈልጎ ሊቆጣ ስለሚችል የእግዚአብሄርን ፅድቅ የመስራት አቅም ይጎድለዋል፡፡
ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን? የያዕቆብ መልእክት
2፡4
4.
የሰው ቁጣ ትክክለኛውን የመቅጫና የመታገሻን ጊዜ አይለይም፡፡ የሰው
ቁጣ ትክክለኛውን ጊዜ ስለማይለይ የእግዚአብሄርን ፅድቅን የማምጣትን አላማ ግቡን አይመታም፡፡
ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም
ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡5
5.
ሰው በሃይሉ ስለማይበረታ እግዚአብሄር የሌለበት ቁጣ ፍሬ የለውም
እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤
ሰው በኃይሉ አይበረታምና። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡9
6.
የሰው ቁጣ ለእግዚአብሄር ቁጣ ስፍራን ስለማይተው አይሳካተለትም
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል
የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡19
7.
የሰው ቁጣ ዋናውን የስራውን ባለቤት እግዚአብሄርን ከውሳኔ የማግለል
ዝንባሌ ስላለው አይከናወንም፡፡
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው
ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን
አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ቁጣ #ፅድቅ #ሃይል #ጥበብ #ልብ #መዳን #እምነት #መንንፈስንአታጥፉ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት
#ፅናት #መንፈስ #መንፈስቅዱስ
No comments:
Post a Comment