የእምነታችንንም
ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ወደ ዕብራውያን 12፡2
ህይወት ሩጫ ነው፡፡ የህይወት ሩጫ አሸናፊነታችን
የሚለካው በምናተኩርነት ነገር ላይ ነው፡፡ በትክክለኛ ነገር ላይ ካተኮትን ሩጫውን በድል እንወጣዋለን፡፡ ትክክለኛውን ነገር ካልተመለከትን
ሩጫውንም መጨረስም ሆነ አሸናፊ መሆን እንችልም፡፡
ኢየሱስን ተመልከተን እንድንሮጥ በኢየሱስ ላይ
እንድናተኩር መፅሃፍ ቅዲስ ያስተምረናል፡፡
ነገር
ግን በህይወት እኔን ስማኝ ፣ በእኔ ላይ
አተኩር የሚሉ ብዙ ተፎካካሪ ነገሮች አሉ፡፡ እኔን ካልተመለከትክ አይሳካልህም፡፡ እኔን ካለሰማህ ዋ የሚሉ የሚያስፈራሩ
ብዙ ነገሮች በዙሪያችን አሉ፡፡ አንዳንዶቹ እኔን ካጣህ ዋጋ የለህም ብለው ያስፈራራሉ፡፡ እኔን ካገኘህ ህይወትህ ይለወጣል ብለው
ካላቅማችው ቃል የሚገቡ ብዙ ነገሮች ናቸው፡፡
ሰው
በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር ላይ ማተኮር አይችልም፡፡ ኢየሱስ ላይ ብቻ በማተኮር ሮጠን ይድሉን እክሊል ከተጎናፀፍን ማተኮር የሌሉብንን
ነገሮች ከእግዚአብሄር ቃል እንመልከት፡-
1.
በደስታ እና በሃዘን ላይ ማተኮር ትኩረታችንን ከኢየሱስ ላይ እንድንመልስ ያደርጋል፡፡
ደስታም ሆነ ሀዘን ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ የትኛውንም ደስታ አይናችንን ከኢየሱስ ላይ እንድናነሳ እንዲያደርገን መፍቀድፍ
የለብንም፡፡ እንዲሁም የትኛውም ሃዘን በኢየሱስ ላይ እንዳናተኩር ለማድረግ ከተሳካለት ተሸንፈናል፡፡
የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ
በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡30-31
2.
አድናቆትና ትችት ላይ ማተኮር አይናችንን ኢየሱስ ላይ እንዳናተኩር ያደርጋል፡፡
የሰው አድናቆት ላይ ልባችንን መጣል የለብንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰው የሚያደንቀንም ሆነ የሚጥለን ስለማያውቀን ነው፡፡
በሰው አድናቆት ላይ ልባችንን ከጣልን ህይወታችንን እንጥላለን፡፡ የሰውን ክፉም ወሬም ይሁን አድናቆት መጠበቅ ያለብን በልባችን
ውስጥ ሳንከት በውጭ ነው፡፡ በክፉ ወሬም ሆነ በመልካመ ወሬ ራሳችንን ማማጠን አለብን፡፡
በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡8
ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም ልብህ ሐሤት አያድርግ፥ መጽሐፈ ምሳሌ 24፡17
አስተማማኙ ደስታ በጌታ ደስ የምንሰኝበት ደስታ ብቻ ነው፡፡ ከጌታ ውጭ ያለው ደስታ ሁሉ ጊዜያዊ ደስታ ነው፡፡
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው
ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ
በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29-31
3.
በክብርም በውርደትም ላይ ማተኮር አደገኛ ነው፡፡
የምድራዊ ክብርም ሆነ ውርደት ልናተኩርባቸውና ልንደገፍባቸው የማንችላቸው ጊዜያዊ ነገሮች ናቸው፡፡
የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና። ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥
ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል። የያዕቆብ መልእክት
1፡9-11
4.
ነገና ትላንት ላይ ማተኮር ኢየሱስ ላይ እንዳናተኩር ያደርገናል፡፡
የእግዚአብሄር ምህረት ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ባለፈው በሰራው በትላንት ላይ ከቆምን ከዛሬ
በረከት ሰላምና ስኬት ጋር እንተላፋለን፡፡ ዛሬን ንቀን ደግሞ በነገ ብቻ ላይ ካተኮርን እንሳሳታለን፡፡ ነገን ጎትተን ዛሬ ላይ
ለመኖር ከፈለግን ነገራችን ይዛባል፡፡
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡34
በጌታ ላይ ማተኮር ትተን በማናውቀው ነገ ላይ ማተኮር ውድቀት ያመጣል፡፡
አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥
ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። የያዕቆብ መልእክት 4፡13
5.
በውድቀትና በስኬት ላይ ማተኮር በኢየሱስ ላይ እንዳናተኩር ይሸፍነናል፡፡
ውድቀት ላይ ማተኮር ኢየሱስን ተመልከተን ሩጫችንን በትግስት እንዳንሮጥ ሊያግደን ይችላል፡፡ ከውድቀታችን ተምረን እንደገና
ኢየሱስ ላይ ማተኮር ግን ወደፊታችንን ያሳምረዋል፡፡ እግዚአብሄር ከማንም ጋር ውድድር ውስጥ አይገባም፡፡ እግዚአብሄር ሆን ብሎ
ለመጣል ብሎ ማንንም በክፉ አይፈትንም፡፡ እግዚአብሄር ከውድቀታችን የሚጠቀመው ነገር ትሁት መሆናችን ራሳችንን ይበልጥ ማወቃችንና
ለመስማት መዘጋጀታችንን ብቻ ነው፡፡
እንዲሁም በስኬት ላይ ማተኮራችን ትልቁን የእግዚአብሄርን አላማ እንዳናይ ያደርገናል፡፡ ስኬትን የሚሰጠን እግዚአብሄር
ላይ እንጂ ስኬቱን ላይ ካተኮርን መውደቃችን አይቀርም፡፡ ያለፈው ስኬታችን ላይ ካተኮርነና በስኬታችን ከተኩራራን የሚበልጠውን የወደፎረቱን
ስኬት ለመያዝ እናዳንዘረጋ ጠላት ይሆንብናል፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ
ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡13
6.
በድካማችንም ይሁን በጥንካሬያችን ላይ ማተኮር እንዲሁ ሩጫውን በትግስ እንዳንሮጥ እና እንዳንፈፅመው ያግደናል፡፡
ማግኘታችንም ሁሉን
እንድንችል አያደርገንም፡፡ ማጣታችንም ሁሉን እንድንችል አያግደንም፡፡ ማጣትም ማግኘትም ምንም አይደሉም፡፡
መዋረድንም አውቃለሁ
መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡12-13
7.
በሰዎች ላይ ማተኮር
በመልካም ሰዎችም ላይ
ይሁን በክፉ ሰዎች ላይ ማተኮር የብርታታችን ምንጭ በሆነው በክርስቶስ ላይ እንዳናተኩር ያደናቅፈናል፡፡ ሰዎች መልካም የሚሆኑልን
እግዞአብሄር ሲጠቀምባቸው ብቻ ነው፡፡ የሰዎች የመልካምነታችው ምንጭ እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን እንዲሁ ተጠቃሚው
ሰይጣን እንጂ ሰዎች አደሉም፡፡ የበደሉን ሰዎችን ይቅር አለማለት ትኩረታችንን ከኢየሱስ ላይ አንስተን ሰዎች ላይ እንድናደርግ ያደርገናል፡፡
በሰዎች ላይ ማተኮር ውድቀትን ያመጣል፡፡
በህይወታችን ራሳቸውን
ሰጥተው ከሚያገለግሉን ሰዎች አልፈን ካላየን እንሰናከላለን፡፡ ሰዎች በስጦታ ቢያገለግሉን የእግዚአብሄር ስጦታ እንጂ የሰዎች አይደለም፡፡
እኔ ተከልሁ
አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡6-7
8.
በሰይጣን ላይ ማተኮር የእግዚአብሄርን
በጎነት እንዳናጣጥመው ያደርገናል፡፡
ሰይጣንን ምንም እንደማያደርግ
መናቅ መልካም አለመሆኑ ያህል ሰይጣን ላይ ማተኮር መልካመ አይደለም፡፡ ሰይጣን የተሸነፈ
ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የሚሰራው ሰውን በማስፈራራት ስለሆነ ሁልጊዜ ትኩረትን ይፈልጋል፡፡ ትኩረታችሁን ከኢየሱስ ላይ በማንሳታችሁ
ብቻ ሰይጣን ይጠቀማል፡፡
እኛ የምንኖረው በሰይጣን
ምህረት አይደለም፡፡ እኛ የምንኖረው አስኮናኞች ኑሩ ብሎ ሰይጣን ስለፈቀደለን ሳይሆን በተሰጠን በልጅነት ስልጣናችን ተጠቅመን በግድ
ነው፡፡ እኛ የምንኖረው በእግዚአብሄር ምህረት ብቻ ነው፡፡
ስለ ፍርድም፥
የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 16፡11
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ተመልክተን #እይታ #ማጣት #ማግኘት #ትላንት #ነገ #ውድቀት #ስኬት #አድናቆት #ትችት #ደስታ #ሃዘን
#አማርኛ
#ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment