Popular Posts

Monday, September 30, 2019

እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም



ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። ኦሪት ዘዳግም 28፡13-14
ሰው በእግዚአብሄር ክብር የተፈጠረው ለእግዚአብሄር እየተገዛ እንዲገዛ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የበላይ ለሆነው ለእግዚአብሄር እውቅና እየሰጠ የበላይ ለመሆን ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን ብቻ እያመለከ ራስ እንዲሆን ነው፡፡
የመጀመሪያው ሰው አዳም ለእግዚአብሄር በተገዛበት ጊዜ ሁሉ ራስ ነበረ፡፡ አዳም ከእግዚአብሄር ቃል ወደግራም ወደቀኝንም ባላለ ጊዜ የበላይ እንጂ የበታች አልነበረም፡፡
ሰው ለእግዚአብሄር አምላክነት በታዘዘ ጊዜና ለእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ብቻ በሚገዛበት ጊዜ ነገሮች ሁሉ በሙሉ ልባቸው ለእርሱ ይሰሩለት ነበር፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ቃል በታዘዘበት ዘመን ሁሉ ተፈጥሮ እንደ ሃይሉ መጠን ይሰጠው ነበር፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ቃል ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባላለበት ጊዜ ሁሉም ነገሮች ሁሉ ይሰሩለት ይታዘዙት ይሰሙት ነበር፡፡
ሰው አሁንም ለእግዚአብሄር ቃል እውቅና በሰጠ መጠን ነገሮች ለእርሱ እውቅና ይሰጣሉ፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ቃል ልቡን በሰጠ መጠን ነገሮች ለእርሱ ልባቸውን ይሰጡታል፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ቃል ወደቀኝና ወደግራ ሲል ነገሮችም ከትእዛዙ ያፈነግጣሉ፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ቃል ችላ ባለ መጠን ነገሮች ችላ ይሉታል፡፡ ሰው ራሱን ለእግዚአብሄር አምላክነት ባስገዛ መጠን ሁኔታዎች ለእርሱ ይገዙለታል፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙረ ዳዊት 1፡2-3
ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ብቸኛ የህይወቱ መመሪያ ሲያደርግ በሚሰራው ነገር ሁሉ ይከናወንለታል፡፡
ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡7-8
ሰው እንደእግዚአብሄር ቃል ለእግዚአብሄር ከተገዛ እግዚአብሄርን አልፎ የሚገዛው ሌላ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ ሰው ግን ለእግዚአብሄር ስልጣን ካልተገዛ ለሌላ ነገር እንደማይገዛ ምንም ማስተማመኛ አይኖረውም፡፡  
ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። ኦሪት ዘዳግም 2813-14
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ስኬት #ክንውን #መታዘዝ #ስልጣን #ሃይል #መገዛት #መታዘዝ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

No comments:

Post a Comment