እነሆ፥
ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። ማቴዎስ 1:23
እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ፡፡ ከዘላለም የነበረው
የእግዚአብሄር ቃል ስጋ ለበሰ፡፡ ኢየሱስ የሰውን ስጋ በመልበስ ከድንፍግል ማሪያም ተወለደ፡፡
እግዚአብሄር በሰው መካከል አደረ፡፡ ኢየሱስ በእኛ
መካከል ተመላለሰ፡፡ ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሙሉ ለሙሉ ከፈለ፡
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14
የአማኑኤል
በሰው መካከል የመመላለስ ዋናው አላማ ሰዎችን ከሃጢያት ለማዳን ነው፡፡ ሰዎች ከሃጢያት የሚድኑት ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለላቸውን
የሃጢያት መስዋእት ለእኔ ነው ብለው ሲቀበሉ ነው፡፡
ልጅም
ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ማቴዎስ 1:21
የገናን በአል ስናከብር ኢየሱስ የመጣበት ሰውን
ከሃጢያት የማዳን አላማ በህይወቴ ተፈፅሟል ወይ ብለን መጠየቅ በአሉን ትርጉም ያለው በአል ያደርገዋል፡፡
ከሃጢያት ነፃ አልወጣሁም ምን ማድረግ ይገባኛል
የሚል ማንም ሰው ካለ መፅሃፍ ቅዱስ ስለዛ ሰው እንዲህ ይላል፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ለመዳን የሚያስፈልገው ኢየሱስ ስለሃጢያትህ እንደሞተና
በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ ማመንና ኢየሱስን የህይወት ጌታ አድርጎ መሾም ነው፡፡
ይህንን ፀሎት ከልብህ በመፀለይ የእግዚአብሄር
ልጅ አድርጎ እግዚአብሄር እንዲቀበልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡
እግዚአብሄር ሆይ ሃጢያተኛ ነኝ፡፡ የሃጢያት ደሞዝ
ደግሞ ለዘላለም ከአንተ መለየት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሃጢያት ለመዳኛ ያዘጋጀኸውን የሃጢያት መስዋእት ኢየሱስን እቀበላለሁ፡፡ እየሱስ
ስለሃጢያቴ በእኔ ምትክ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለና እንደሞተ ከሞትም እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ላይ ጌታ አድርጌ
እሾመዋለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ዘመን ሁሉ እከተለዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ የዘላለም
ህይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት
#መናገር #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ቃል
#መዳን #ማድረግ
#መስዋእት #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment