በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦ በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ። እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ። እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ። መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ራእይ 3፡14-22
ፍላጎት ማጣት
ሎዶቅያ ቤተክርስትያን የተወቀሰችበት የመጀመሪያው ነገር እግዚአብሄርን መፈለግ ማቆሟ ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ ያቀመችበትም ምክኒያት ሃብታም ነኝ ብላ ስላሰበች ነው፡፡
ሃብት የሚለካው እግዚአብሄርን በመፈለግ ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ በተውን ጊዜ ድሆች ነን፡፡ እግዚአብሄርን በሁሉም የህይወት ክፍላችን መፈለግ እውነተኛ ባለጠጋ ያደርገናል፡፡
የሎዶፂያ ቤተክርስቲያን የተጠራችንው በልታና ጠጥታ ለመኖር ሳይሆን የጌታን በጎነት ለመመስከር ነው የጠፉትን ለመፈለግ ነው ለአለም ብርሃን ለመሆን ነው፡፡ የሎዶቅያን ቤተክርስትያን ግን ምድራዊ ነገሮችን ስላገኘች ደረስኩበት አሁን ምንም አያስፈልግኝም በማለት ከዋናው አላማዋ እግዚአብሄርን ከመፈለግ ተመለሰች፡፡
እግዚአብሄርን የምንፈልገው ስለሚበላና ስለሚጠጣ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምንፈልግው በህይወታችን ስላስቀመጠው አላማ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምንፈልግው የእርሱ ስራ በምድር ሰርተን ጌታን ለማስከበር ነው፡፡ ጌታን የምንፈልገው የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን በመፈለግ ነው፡፡ ጌታን የምንፈልገው የመንግስቱን ወንጌል ለመስበክ ነው፡፡ ጌታን የምንፈልገው ሰዎችን ደቀመዝሙር ለማድረግ ነው፡፡
ይህ ክብራችን ነው፡፡ ይህ ጥሪያችን ነው፡፡ ይህ ህይወታችን ነው፡፡
የእይታ ችግር
ሰው ራቁቱ ሆኖ በልብሱ ከተመካ የጎደለው እይታ ነው፡፡ የሚያስፈልገው ነገሮችን በትክክል ማየት ነው፡፡ የሰው አይን ጤነኛ ካልሆነ ሁለንተናው ይታመማል፡፡ ሰው በትክክል ካላየ ከፍተኛ ችግር ይገጥመዋል፡፡ ሰው እግዚአብሄር እንደሚያያቸው ነገሮችን ካላየን ህይወታችን ይባክናል፡፡ ሰው እግዚአብሄር የሚንቃቸውን ካልናቀ ጌታ የሚያከብራቸውን ካላከበረ ህይወቱ የብከነት ህይወት ነው የሚሆነው፡፡
በዚህ ምክኒያት ኢየሱስን ከሁኔታው አውጥታዋለች፡፡ እኔ እበቃለሁ ኢየሱስ አያስፈልግም ብላለች፡፡ ኢየሱስ በደጅ ቆሞ እያኳኳ ነው፡፡
እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ሎዶቅያ #በራድወይምትኩስ #ድልለነሳው #ጆሮያለውይስማ #አእምሮ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment