ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ያለን ቦታ እንዴት ልዩ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን ክብር እንዴት ድንቅ ነው፡፡ በምድር ላይ ያለን ስልጣን እንዴት ታላቅ ነው፡፡
ለሚያም ሁሉ ይቻላል፡፡ ለሚያምን የማይቻል ነገር የለም፡፡ እምነት የማይፈታው ቁልፍ የለም፡፡ ለሚያምን የሚያቅተው ነገር የለም፡፡ እምነት የማይደርስበት ከፍታ የለም፡፡ እምነት የማይሻገረው ርቀት የለም፡፡ እምነት የማደርስበት ስፍራ የለም፡፡
እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ የእምነት ሃይል ለሁሉም የተሰጠ ነው - ለሚያምን ሁሉ፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡ ሁሉን መቻል እምነት ላለው ሁሉ የተሰጠ መብት ነው፡፡
እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ስለህይወታችን ክፍል እግዚአብሄር የሚለውን መስማት እምነትን ያመጣል፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 1፡17
የእግዚአብሄርን ቃል ሲመጣልን ለቃሉ የመጀመሪያ ስፍራ በህይወታችን በመስጠት ቃሉን ማሰላሰል አለብን፡፡
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያሱ 1፡8
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከቃሉ ስናገኝ ንግግራችን ሁሉ እንደቃሉ መቃኘት ይኖርበታል፡፡ ቃሉን መናገር ይኖርብናል፡፡
ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡13
እንዲሁም ቃሉን ማድረግ አለብን፡፡ ቃሉን ካላደረገን በቃሉ የተባለልን በህይወታችን ሳይሆን ይቀራል፡፡
ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ያዕቆብ 1፡22
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል !
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment