ብዙ ጊዜ እውነት በሃይማኖት ነኝ ብለን እንጠይቃለን፡፡ በህይወት ዘመን ሊመለስ የሚገባው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ብዙ ጥያቄዎችን
መመለስ እንኳን ባንችል ይህን በሃይማኖት ነኝን የሚለው ጥያቄ ከመለስን ይበቃል፡፡
በሃይማኖት መኖራችን ዘላለማችንን የት እንደምናሳልፍ ይወስነዋል፡፡ በሃይማኖት ብንኖር ለዘላለም ከእግዚአብሄር ጋር እንኖራልን፡፡
በሃይማኖት ካልኖርን ለዘላለም ከእግዚአብሄር ተለይተን ለሰይጣንንና ለመላእክቱ በተዘጋጀው እሳት ባህር ውስጥ እንጣላለን፡፡
ግን በሃይማኖት መሆናችን እንዴት ይታወቃል? በሃይማኖት ለመኖር ምንድ ነው ብቁ የሚያደርገን? እግዚአብሄርን ለማስደሰት
ብቃትን የሚሰጠን ምንድነው ?
የማናችንም አስተያየት እዚህ ጋር አይሰራም፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ለዚህ መልስ አለው፡፡
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ
ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5
እየሱስ ስለሃጢያቴ ሞቷል በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ብሎ የሚያምንና እየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚመሰክር
ሰው እግዚአብሄር ይቀበለዋል፡፡ እየሱስም በውስጡ መኖር ይጀምራል፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ብቁ የሚያደርገን የራሳችን መልካም ስራ ሳይሆን እየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የከፈለውን ዋጋ ለእኔ ነው እየሱስ
የሞተው በእኔ ምትክ ነው ብለን እየሱስን ወደልባችን መቀበላችን ነው፡፡ ብቃታችን እየሱስ በልባችን በውስጣችን መኖሩ ነው፡፡
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ
ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5
No comments:
Post a Comment