I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Friday, June 3, 2016
መዝሙርን ዘፈን ያላደረገው
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዘፈን ሃጢያት ነው ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ብዙዋቻችንን ሲያነጋግር ቆይቶዋል፡፡ እኔም በልቤ ያለውን የሚሰማኝን ዘፈን ሃጢያት ነው በሚል ርእስ ፅሁፍን ፅፌ ነበር፡፡
እግዚአብሄር መዝሙርን እንደሚፈልግ ዘፈንን ግን እንደማይፈልግ እንዲያውም ዘፋኝነት የስጋ ስራ እንደሆነ እነዚህን የሚያደርጉም የእግዚአብሄርን መንግስት እንደማይወርሱ መፅሃፍ ስለዘፈን ጎጂነትር በአፅንኦት ይናገራል፡፡
እግዚአብሄር ዘፈንን ለምን ጠላ መዝሙርንስ ለምን ወደደ? የሚለውን ለመመለስ መዝሙር ከዘፈን የሚለይበትን ነገሮች ማወቅ ግድ ይላል፡፡
መዝሙር እንደ ማንኛውም ዘፈን በግጥም በዜማ የሚሆን እንጉርጉሮ ቢሆንም እንዲሁም መዝሙርንም ዘፈንም የምንጫወትበት መሳሪያ ተመሳሳይ ቢሆንም መዝሙርን ዘፈን የማያደርገው ብዙ ወሳኝ መሰረታዊ ነገሮች አሉት፡፡
መዝሙርን ዘፈን ያላደረገው
1. የመዝሙር አላማ ሰዎች በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠሩ ክቡራን እንደሆኑና ሰይጣንን ሰምተው በሃጢያት እንዳይዋረዱና ከንቱ እንዳይሆኑ እግዚአብሄር እንደ ፈጠራቸው የክብር ደረጃ እንዲኖሩና ማስተማር ነው፡፡
2. የመዝሙር አላማ ሰዎች እግዚአብሄር በክርስቶስ የከፈለላቸውን የሃጢያት ዋጋ እንዲረዱና ክርስቶስ ለእነርሱ እንደሞተላቸው እነርሱ ደግሞ ለሃጢያት ሞተው ለክርስቶስ እንዲኖሩ የሚያበረታታ ነው፡፡
3. የመዝሙር አላማ ሰዎች የህይወት ጠላት የሆነውን ዲያቢሎስን እና ስራውን ከህይወታቸው እንዲክዱ ልቅነትንና ሃጢያትን እንዲፀየፉ ራስን እንዲገዙ ማበረታታት ነው፡፡
4. የመዝሙር አላማ ሰዎች በጊዜያዊ የአለም ደስታ ዘላለማዊ ህይወታቸውን እንዳያጡ የዘላለም ህይወታቸውን አጥብቀው እንዲይዙ ለማበረታታት የታለመ ነው፡፡
5. የመዝሙር አላማ ሰዎች በምድር ላይ ጊዜያዊ ተላላፊ ምፅአተኛ እንደሆኑ አውቀው በአለም ጉድፍ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መምከር ነው፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤1ኛ ጴጥሮስ 2፡11
6. መዝሙር ሰዎች ለፈጠራቸው ባለቤታቸው ለሆነውና ዘወትር ክብር ለሚገባው ለእግዚአብሄር ክብር እንዲሰጡ የሚመራ ነው፡፡
7. መዝሙር እግዚአብሄርን ከምንም በላይ እንዲያከብሩና እርሱን ለማስደሰት እንዲኖሩ የስጋ ምኞታቸውንና የነፍሳቸውን ክፉ ፍላጎት እንቢ እንዲሉ እግዚአብሄርን ለማሳየት የሚዘመር ነው፡፡
8. መዝሙር እንካ በእንካ ያልሆነን ከራስ ወዳድነት የፀዳ ልጁን እየሱስን ለእኛ በመስጠት ያሳየውን የእግዚአብሄርን እውነተኛ ፍቅር የሚገልፅ ነው፡፡
9. እውነተኛ ሰላም የሚገኘው ለእግዚአብሄር አምላክነት ስንገዛና እግዚአብሄ የፈጠረንን አላማ ስንከተል ብቻ እንጂ በተለያየ ቁሳቁስና ልምምድ የማይመጣ መሆኑን የሚያሳይ መዝሙር ነው፡፡
https://www.facebook.com/abiy.wakuma
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment