በህይወቴ ካገኘሁዋቸው ሰዎች ሁሉ ህይወቱን መለወጥ የማይፈልግ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ሁሉም ሰው ህይወቱን ወደተሻለ መለወጥ ይፈልጋል፡፡
ታዲያ ህይወታችንን መለወጥ እየፈለግን ህይወታችንን እንደፈለግነው መለወጥ ያልቻልነው ለምንድነው የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ጥያቁ ነው፡፡
ለዚህ የተለያዩ ምክኒያቶችም ቢኖሩ በአገልግሎት ህይወቴ የተመከትኩትን ዋና ምክኒያት ላካፍላችሁ፡፡ ብዙ ሰዎች መለወጥ ይፈልጋሉ ነገር ግን ስለህይወታቸው ሃላፊነት መውሰድ በፍፁም አይፈልጉም፡፡
1. ስላልተለወጠው ህይወታቸው የሚያሳብቡበት ነገር አለ፡፡ እከሊት ነች ፡ እከሌ ነው ፡ ወላጆቼ ናቸው አገሩ ነው ፡ አለቃዬ ነው ለዚህ ያበቃኝ ስለሚሉና ጥፋቱን በሌላው ላይ ስለሚያላክኩ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡
2. ወደፊትም መለወጥ የማይችሉበትን ምክኒያቶችን ይዘረዝራሉ፡፡ የማልለወጥበት ምክኒያት ጊዜው ነው ፡ አገሩ ነው ፡ ሰዉ ከፍቶ ነው በማለት ለህይወት ለውጣቸው ሃላፊነቱን ከመውሰድ ይልቅ በቀላሉ ጥፋቱን ወደሌላ በማላከክ ጥሩ ሰበብ አግኝተው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ አሉታዊ ነገሮች እያሉ ሌሎች ሰዎች ህይወታቸውን ይለውጣሉ፡፡ እነዚህ የተለወጡት የተሸነፉ ሰዎች የሚያከብሩዋቸው ምክኒያቶች ህይወታቸውን ሊያስቆም የሚችል በቂ ምክኒያት እንደሆነ አልተቀበሉትም፡፡
ህይወት ጥቂቱ በመቶ በውጭ ሁኔታ ለምሳሌ ሰዎች በእኛ ላይ በሚያደርጉት ሲወሰን አብዛኛው በመቶው ግን የሚወሰነው እኛ ለዚያ ነገር በምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡ ምርጫው የእኛ ነው፡፡ በሁኔታው ተስፋ ልንቆርጥ ወይም ብንወድቅ እንኳን ወድቀን እንደ ማንቀር በማመን መነሳታችንን ማየት እንችላለን፡፡
ሁላችንም ብዙ ነገሮች እንዳናደርግ ብዙ ምክኒያቶች ነበሩን፡፡ ነገር ግን የቀጠልነው ምክኒያቶቹ በህይወት ተስፋ ለመቁረጥ በፊታችን በቁ ስላልሆኑ ነው፡፡ ከእነዚህ ያነሱ ምክኒያቶች እንኳን ብዙ ሰዎችን ከእርምጃቸው አሰናክለዋል፡፡
አንተ በህይወትህ ተስፋ ከቆረጥክ ሌላ ማንም ሰው ሊረዳህ አይችልም፡፡ አንተ ግን ከተነሳህ ሌላ ሰው ቢረዳህም ባይረዳህም ህይወትህን ይለወጣል፡፡
ያንተ ህይወት እንዲለወጥ ያንተ አስተዋፅኦ እጅግ ወሳኝና አብዛኛው ማጆሪቲ /majority/ ነው፡፡ ያንተ ህይወት ያንተ ነው፡፡ ሰዎች ህይወትህን ሊለውጡ በፍፁም አይችሉም፡፡ ለህይወትህ መለወጥ ጥቂት አስተዋፅኦ ብቻ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ህይወትህ እንዲለወጥ ሃላፊነትን ውሰድ፡፡
ህይወትህ ለመለወጥ የሚያስፈልገውን ለማድረግ ተነስ
ህይወትህን ለመለወጥ አቅድ እርምጃም ውሰድ
ከዚህ ሁሉ በላይ እግዚአብሄር መልካም እንደሆነና ከሃጢያትህ ሊያድንህ ልጁን በመስቀል ላይ የከፈለልህ ስለሚወድህ መሆኑን አውቀህ በእርሱ ታመን፡፡
No comments:
Post a Comment