የከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል ሰባኪው
በኢየሩሳሌም የነገሠ የሰባኪው የዳዊት ልጅ ቃል። ሰባኪው። ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል። ከፀሐይ በታች መክብብ 1፡1-3
አይገርምም ሰባኪው ሁሉ ከንቱ ነው ንፋስን እንደመከተል ነው ይላል፡፡ እውነት ነው ከፀሃይ በታች ሁሉ ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ፡፡
ሰባኪው ከፀሃይ በታች ምን ምን ከንቱ እንደሆነና ምንም ዋጋ እንደሌለው የሚናገረው ስለምን እንደሆነ እንመልከት፡፡
ከእግዚአብሄር የተለየ የሰው ጥበብ ከንቱ ነው፡፡ መክብብ 2፡14-16
በእግዚአብሄር ያልሆነ መስራት መልፋትና መድከም ከንቱ ነው፡፡ መክብብ 2፡14-16
እግዚአብሄር የሌለበት ነገሮችን ማከማቸት ንፋስን እንደመከተል ነው መክብብ 2፡26
ካለአላማ መኖር ከእግዚአብሄር ጋር ያልተዛመደና ያልተገናኘ ህይወት ራሱ ከንቱ ነው፡፡ መክብብ 3:18–22
በአለም ያለ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ውድድርና ቅንአት ከንቱ ነው፡፡ መክብብ 4:4
በስግብግብነት ያለቅጥ መስራት ከንቱ ነው፡፡ መክብብ 4:7-8
ሃይልና ለስልጣን ማከማቸት ከንቱነት ነው፡፡ መክብብ 4:16
ስስት ፡ ምኞትና አለመርካት ከንቱ ነው፡፡ መክብብ 5:10
የማይጠቀሙበት ሃብትና ቅንጦት ማከማቸት ንፋስን እንደመከተል ነው፡፡ መክብብ 6:1-2
ሰው በሰማይ አምላክ በእግዚአብሄር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ከእግዚብሄር ጋር ህብረት ማድረግ እንዲችል በመልኩና በአምሳሉ ተፈጥሮአል፡፡ሰው ለፈጣሪው ለእግዚአብሄር እውቅና በመስጠትና እርሱን በመፍራት በምድር ላይ ያዘጋጀለትን መልካም ስራ እንዲያደርግ ተፈጥሮአል፡፡
ሰው ከተፈጠረለት አላማ ውጭ ሲኖር ሁሉ ከንቱ ነው፡፡
ከዚህ ውጭ የሆነ ነገር ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት ሲኖረን ነው እንጂ ፣ ከእግዚአብሄር ጋር ስንሰራ ነው እንጂ ፣ ለእግዚአብሄር ስንኖር ነው እንጂ እግዚአብሄርን ስናገለግል ነው እንጂ ከዚያ ውጭ ከፀሃይ በታች ያለ ነገር ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ከእግዚአብሄር ውጭ ህይወት ትርጉም የለውም፡፡
ከእግዚአብሄር ውጭ ህይወት ዋጋ የለውም፡፡ሰው ለህይወቱ ትርጉም የሚያገኘው ለፈጠረው ለእግዚአብሄር እውቅና ሲሰጥና ለእርሱ ለመኖር ሲወስን ብቻ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment