Popular Posts

Thursday, June 23, 2016

የስኬት ጣራ

ሁላችንም በክርስትና ህይወታችን ማደግና የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረስ እንፈልጋለን፡፡ 

የክርስትና ህይወት የእድገት ጫፍ ጣራው ምንድነው ? የሚለውን ጥያቄ መልስ ማወቃችን ደረጃው ላይ ስንደርስበት ያሳርፈናል በክርስትና የሚያስቀና ሰው ሚሊየነር የሆነ ሰው አይደለም፡፡

በክርስትና የሚያስቀና የመጨረሻው ሰው በሚሊየኖች ሰዎች ታዋቂ የሆነ ዝነኛ ሰው አይደለም፡፡ 

በክርስትና እርሱን ባደረገኝ ተብሎ የሚቀናበት ሰው ከሰው ሁሉ በላይ ሃያል የሆነ ሰው አይደለምን፡፡

በክርስትና ፐ የሚባልለትና የሚያስቀና ሰው የመጨረሻው ስኬታማና የተከናወነለት ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ እግዚአብሄርን በመምሰል ጌታን የሚከተልና የሚያገለግል ሰው ነው፡፡

በክርስትና ከዚህ ደረጃ በላይ ደረጃ የለም፡፡ ይህ ለእግዚአብሄርም ለእኛም በቂ ነው፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ . . . ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6 ፣ 8
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

No comments:

Post a Comment