Popular Posts

Saturday, June 25, 2016

የማይታይ እጅ

ስለ እግዚአብሄር አሰራር የማይረዳ ሰው ይህን እድሌ ነው ይላል፡፡ እኛ ግን እግዚአብሄር ነው እንላለን፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
እግዚአብሄር እኛን ሁላችንን ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር ለህይወታችን የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እኛ ለህይወታችን የማንፈልገው ነገር እንዳለ ሁሉ ደግሞ እግዚአብሄርም ለህይወታችን የማይፈልገው ነገር አለ፡፡ ይህንን ምክሩን ለማስፈፀም እግዚአብሄር ምድርንና ሰማይን በሚገባ እየተቆጣጠረ እየመራ ነው ፡፡
ሰው በራሱ በልቡ ያለውን ነገር ሁሉ ቢያደርግ አለም ምን ልትሆን እንደምትችል መገመትም ያስቸግራል፡፡
በሰው ልብ ብዙ ሃሳብ ቢኖርም መጨረሻ ላይ የሚያይለውና የሚበረታውና የሚፈፀመውም የእግዚአብሄር ሃሳብ ነው፡፡
ይህን ማወቅ እንዴት ያሳርፋል፡፡ ምንም እንኳን በሰው ልብ ውስጥ ያለው ሃሳብ ብዙ ቢሆንም ግን በርትታ የምትወጣውና የምትፈፀመው የመልካሙ የአባታችን የእግዚአብሄር ሃሳብ መሆኑን ማወቅ እጅግ ደስ ያሰኛል፡፡
ይህንኑ ሃሳብ በብሉይ ኪዳን ቋንቋ እንዲህ በማለት ሰባኪው ይገልፀዋል ፡፡
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11
ይገርማል እግዚአብሄር አይሆንም ካለ የሩጫ ድል ለፈጣን አይሆንም፡፡
እግዚአብሄር ካልሰጠ ባለጠግነት በቅልጥፍና አይመጣም፡፡
እግዚአብሄር ይሁን ካላለ ሰው አዋቂነቱ ብቻ ሞገስን አይሰጠውም፡፡
ሁሉን የሚሰካካው የሚያገናኘው የጊዜና የእድል ባለቤቱ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21

No comments:

Post a Comment