Popular Posts

Follow by Email

Monday, June 27, 2016

የሚያስፈልጋችሁን

እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡31-32
 
እግዚአብሄር የሚያዘጋጀው የሚያስፈልገንን ነው፡፡ በሚያስገልገን መጠን ነው እግዚአብሄር የሚያቀርበው፡፡ 
 
እግዚአብሄር ተረፍ አድርጎ ካቀረበና አሁን ከሚያስፈልገን በላይ ከሰጠን እንኳን ያ ማለት ሌላ የሚያስፈልገን ነገር እየመጣ ነው ማለት ነው፡፡ 
 
ተረፍ ብሎ ካልመጣ ደግሞ እግዚአብሄር ይመስገን ፍላጎት የለብንም ማለት ነው፡፡
 
እግዚአብሄር የሚያቀርበው እንደፍላጎታችን መጠን እንጂ እንደ ጎረቤታችንም አይደለም፡፡ የእኛና የጎረቤታችን ፍላጎት ይለያያል፡፡ እግዚአብሄር ለእኛና ለጎረቤታችን እኩል አያቀርብም፡፡ 
 
የእኛ አቅርቦት ከጎረቤታችን ከበለጠ ያ ማለት ይበልጥ ፍላጎት እየመጣብን ነው ማለት ነው፡፡ የጎረቤታችን ከእኛ ከበለጠ ደግሞ ጎረቤታችን የሚያስፈልገው ሁኔታ ላይ ነው ማለት ነው፡፡ 
 
ፅድቁንና መንግስቱን ስንፈልግ ምን እንደሚያስፈልገን የሚያውቅና የሚሰጥ አባት ማግኘትን የመሰለ ነገር የለም፡፡ 
 

No comments:

Post a Comment