Popular Posts

Thursday, June 30, 2016

ታመን

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፡፡ ምሳሌ 3፡5

ህይወት የእግዚአብሄር ውድ ስጦታ ነው፡፡ ይህን ስጦታ በሚገባ መያዝና መጠቀም ማስተዋል ይጠይቃል፡፡ የህይወትን ስጦታ በሚገባ ለመጠቀም ወደ ሰጭው መመለስና ለምን እንደሰጠንና ምን እንድናደርግበት እንደሰጠን መረዳት ይጠይቃል፡፡

በሌላ አነጋገር በምድር ላይ ለእግዚአብሄር ክብር ለመኖር ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ምሪት ላይ መደገፍ ይጠበቅብናል፡፡


የእግዚአብሄርን ስጦታ ህይወትን በራስህ ማስተዋል አትኖረውም፡፡ የእግዚአብሄርን የህይወት ስጦታ በእግዚአብሄር እውቀትና ምሪት መጠቀም ይጠይቃል፡፡

ሁል ጊዜ በራሳችን እውቀትና ማስተዋል ነገሮችን ለማድረግ እንፈተናለን፡፡ ነገር ግን የራሳችን ማስተዋል ያስተናል እንጂ የትም አያደርሰንም፡፡

አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር፦ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው። ኢሳያስ 55፡8-9

በእግዚአብሄር የምትታመነውና የምትደገፈው ለእግዚአብሄር አዋቂነትና ፍፁም መሪነትና እውቅና በመስጠት ነው፡፡ ይህን በማለት ለእግዚአብሄር እውቅና ልንሰጥ ይገባናል፡፡

• እኔ ከመፈጠሬ በፊት ለእኔ ያቀድከው ሃሳብ አለ
• የእኔ የህይወት እቅድና ንድፍ በአንተ ዘንድ አለ
• እኔ ለራሴ ከማውቀው በላይ አንተ ለእኔ ታውቃለህ
• አንተ ለእኔ ያለህ አላማ የፍቅር አላማ ነው
• አንተ ለእኔ የምታስበው ሃሳብ መልካም ብቻ ነው

በማለት ይህንን እግዚአብሄር ለህይወታችን ያለውን ሃሳብ ከእግዚአብሄር መፈለግና መከተል መንገዳችን እንዲቃና ያደርጋል፡፡

ምሳሌ 3፡6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።

ለተጨማሪ ፅሁፎች

No comments:

Post a Comment