ይገርማል ፡፡ ሰይጣን በህይወታችን መግቢያ ካገኘ ስፍራ የሰጠነው እኛ ነን ማለት ነው፡፡ ምክኒያቱም እየሱስ በመስቀል ላይ ሲሰቀል የሰይጣንን ሃይልና ስልጣን ሁሉ ገፎታል፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 2፡13-14
ሰይጣን በህይወታችን ስፍራ የሚያገኘው እኛው ከሰጠነው ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ በግድ ምንም ስፍራ ሊወስድ አይችልም፡፡
ሰይጣን በምድር ላይ ለእግዚአብሄር እየኖርን የእግዚአብሄርን ስራ እንድንሰራ በፍፁም አይፈልግም፡፡ ቢችል ከምድረ ገፅ ያጠፋናል፡፡ እኛ የምንኖረው በሰይጣን ምህረት አይደለም ፡፡ ሰይጣን ስለፈቀደልንና አስኮናኞች ኑሩ ብሎ ስለተወን አይደለም የምንኖረው ፡፡
ለእግዚአብሄር የምንኖረውና እግዚአብሄርን የምናገለግለው በሃይልና በስልጣን ነው፡፡
ግን ደግሞ ከፈቀድንለት እንደፈቀድንለት መጠን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ወደህይወታችን ይመጣል፡፡ ዮሃንስ 10፡10
ግን ለሰይጣን ስፍራ መስጠት ማለት ምን ማለት ነው?
ለሰይጣን ስፍራን መስጠት ልብን በንፅህና አለመጠበቅ ነው፡፡
ሰው በቁጣው ላይ ፀሃይ ሲገባና ምሬት ውስጥ ሲገባ ያ በህይወቱ ለሰይጣን በርን ይከፍታል፡፡ ሰይጣን በሰዎች ህይወት የሚሰራው ጥላቻን በህይወታቸው ሲያገኝ ብቻ ነው፡፡
ሰይጣን በሰዎች ህይወት የሚሰራው ሰዎች ፍቅርን ጥለው በራስ ወዳድነት ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡
ቆሻሻ ዝንብን እንደሚጠራ ሁሉ ጥላቻና ራስ ወዳድነት ሰይጣንን ይጠራል፡፡ ጥላቻና ፍቅር ማጣት ለሰይጣን መራቢያ ለም መሬቱ ነው፡፡ ምሬትንና ጥላቻን ከህይወታችን ካስወገድን በህይወታችን ለሰይጣን ስፍራን እንከለክለዋለ፡፡
ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን 4፡26-27
No comments:
Post a Comment