Popular Posts

Follow by Email

Friday, June 10, 2016

መንግስትን ሊሰጣችሁ

አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ። ሉቃስ 12፡32

በህይወት በጣም የምንጨነቅባቸውና ብዙውን ጊዜያችንን እንድናጠፋባቸው የምንፈተንባቸው ነገሮች የኛ ሃላፊነት ያልሆኑ እኛን የማይመለከተንና ጊዜያችንን በከንቱ የሚጨርሱ ለኛ የማይመጥኑ ነገሮች ናቸው፡

በተለይ መፅሃፍ ቅዱስ የኑሮ ሃሳብና የባለጥግነት ምኞት የእግዚአብሄር ቃል በውስጣችን ሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ እንደሚያንቀው ይናገራል፡፡

የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19

እነዚህ ነገሮች እግዚአብሄር ለእኛ ካለው የእገዚአብሄር ልጅነት የነገስታት ቤተሰብ አባልነት ደረጃ አንፃር ሲተያዩ ምንም ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች እግዚአብሄር በህይወታችን ካየልን ደረጃና ግብ ጋር ሲነፃፀሩ ተራና ጥቃቅኖች ናቸው፡፡ እነዚህ ለእኛ ደረጃ የሚያስፈሩም ሆነ እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም፡፡

ደረጃችን የእግዚአብሄር መንግስት ተወካይነት ነው፡፡ ደረጃችን የእግዚአብሄርን መንግስት ጥቅም ማስከበር እንጂ ስለሚበላና ስለሚጠጣ መጨነቅ ለክብራችን አይመጥንም፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡33
ስለዚህ ነው አየሱስ እንዲህ ይላል፡፡

አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ። ሉቃስ 12፡32


No comments:

Post a Comment