Popular Posts

Monday, November 25, 2019

የሚበልጥ አላማ


ከእኛ መካከል ራሱን የፈጠረ ማንም የለም፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሄር ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ የተፈጠረንበት አለማ ከመፈጠራችን በፊት ነበር፡፡ የተፈጠረነው የተፈጠርንበትን አላማ ለማሳካት ነው፡፡ ወደምድር የመጣነው የተፈጠርንበትን አላማ ለማስፈፀም ነው፡፡
ከእግዚአብሄር አላማ የሚበልጥ ምንም ነገር በምድር ላይ የለም፡፡
በምድር ላይ ያለው ነገር ሁሉ የእግዚአብሄርን አላማ ለማስፈፀም የተሰራ ነገር ነው፡፡ በምድር ላይ ያለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሄር አላማ ተስርቷል እንጂ የእግዚአብሄር አላማ በምድር ላይ ላለው ነገር አልረተሰራም፡፡
የእግዚአብሔር አላማ ከደስታችን ይበልጣል
ደስ ሊለን የሚገባው በህይወታችን የእግዚአብሄርን አላማ ስናደርግ ብቻ ነው፡፡ ደስ ሊለን የሚገባው ከእግዚአብሄር አላማ በተቃራኒ ባለመሄዳችን ነው፡፡ ደስ ሊለን የሚገባው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን በመፈፀም እግዚአብሄርን ስናስደስተው ነው፡፡ ከእግዚአብሄር አላማ በተቃራኒው በመሄድ የሚገኝን ጊዜያዊ ደስታ መናቅ አለብን፡፡
ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። ወደ ዕብራውያን 11፡25-26
የእግዚአብሔር አላማ ከክብራችን ይበልጣል
በእግዚአብሀረ መልክና አምሳል በእግዚአብሀረ ክብር ተፈጥረን ነበር፡፡ በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄ ክብር ወድቀን ለዘላለም ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይተን ነበር፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በሰራው የደህንነት ስራ ምክኒያት የእግዚአብሄር  ልጆች ሆነናል፡፡ አሁን ክብራችን እግዚአብሄር ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ቤተሰብ ውጭ ክብር የለንም፡፡ ከእግዚአብሄር አላማ ውጭ ክብር የለንም፡፡   
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። የሐዋርያት ሥራ 20፡24
የእግዚአብሔር አላማ ከፈቃዳችን ይበልጣል
በህይወት የምንወደው እና የምንፈልገው ነገር አለ፡፡ የምንወድውንና የምንፈልገውን ነገር የምንፈልገው ከእግዚአብሄር አላማ ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር አላማ ጋር የተጋጨ እለት የምንፈልገውን ነገር አንፈልገውም የምንወደውን ነገር አንወደውም፡፡
ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22፡42
የእግዚአብሔር አላማ ከምቾታችን ይበልጣል
አንድን ነገር የምናደርገው ስለሚመቸን ወይም ስከለማይመቸን አይደለም፡፡ አንድን ነገር የምናደርገው የእግዚአብሄር አላማ ስላበት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ከሌለበት ምንም ምቹ ነገርን ምቹ ስለሆነ ብቻ አናደርገውም፡፡ ለእኛ የመጨረሻው የምቾት ቦታ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ቦታ ነው፡፡  
እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው። ኦሪት ዘጸአት 3315-16
የእግዚአብሔር አላማ ከእኔነታችን ክብር ይበልጣል
የእኛ ኑሮ ለሞተልን ለእርሱ ነው፡፡ የሞተልንም ለሞተልን እንጂ ወደፊት ለራሳችን እንዳንኖር ነው፡፡ ከእርሱ ክብር የተለየ ክብር የለንም፡፡ ከእርሱ አላማ የሚበልጥ አላማ የለንም፡፡
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡15
እርስ በእርስ ከምንቀባበለው ክብር ይበልጥ የምንፈልገው ከአንዱ ከእግዚአብሄር የሚገኘውን ክብር ነው፡፡
እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? የዮሐንስ ወንጌል 5፡44
የእግዚአብሄር አላማ ከተቀባይነት ይበልጣል
የእግዚአብሄር አላማ ከሰው ከምናገኘው እሺታ እና ተቀባይነት ይበልጣል፡፡ ሰው ቢቀበለን ባይቀበለምን እግዚአብሄር ከተቀበለን ይበቃናል፡፡  
ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ወደ ገላትያ ሰዎች 1፡10
የእግዚአብሔር አላማ ከዝናችን ይበልጣል
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡8-9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #አላማ #እቅድ #ግብ  #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment